በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለይቶ ማቆያ ለሚያገለግሉ ሠራተኞች የበዓል ስጦታ ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 14/2012(ኢዜአ) የለይቶ ማቆያ ኳራንቲን ቦታዎች ንኡስ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተዘጋጀ የለይቶ ማቆያ ቦታ የተለያዩ አገልግሎት ለሚሰጡ ሠራተኞች የበዓል ስጦታ አበረከተ።

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና የንኡስ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ አዳነች አበቤና የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ ወይዘሮ ፈይሰል አብዱላሂ ዛሬ በቦታው ተገኝተው ሠራተኞቹን አመስግነዋል።

ንኡስ ኮሚቴው በዚህ ወቅት ስምንት በግና ፍየሎችን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ባሉበት ያስረከበ ሲሆን ስጦታውን የሰጠው በቀጣይ የሚከበረውን 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል ምክንያት በማድረግ ነው።

የበዓል ስጦታው በዩኒቨርሲቲው ቅጥር ግቢ በተዘጋጀው የለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በማገልገል ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች፣ የጸጥታ ሰራቶኞች፣ የፅዳት ሰራተኞችና በተያያዥ ሙያ ለተሰማሩ የተበረከተ ነው።

ሠራተኞቾ የኮቪድ-19ን ለመከላከል በሚደረገው ሥራ ላይ እየሰጡ ላሉት አገልግሎት ባለስልጣናቱ አመስግነዋል።

ሰራተኞቹ ለሚሰጡት አገልግሎት መንግስት ከጎናቸው እንደሚሆን ገልጸው፣ በቀጣይም ለሃገራቸው እየከፈሉት ያለውን መስዋዕትነት አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

በዓሉን በአካል ቢራራቁም በልባቸው ተቀራርበው ማክበር እንደሚችሉም አስገንዝበዋል።

Related posts

Leave a Comment