ትምህርትሚኒስቴር ከ350 ሺህ በላይ ግምት ያለው ምግብና አልባሳት ለአቅመደካሞችና አረጋዊያን ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22/2012( ኢዜአ) ትምህርትሚኒስቴር ከ350 ሺህ በላይ ግምት ያለው ምግብና አልባሳት ለ200 አቅመደካሞችና አረጋዊያን ድጋፍ አደረገ።

ድጋፉ ለ200 አቅመ ደካሞችና አረጋዊያን አልባሳትን ጨምሮ ለአንደ ወር የሚሆን የምግብና ንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ  ነው።

ድጋፉን የተቀበሉት በአዲስ አበባ የአራዳ ክፍለ ከተማና የወረዳ ዘጠኝ አመራሮችና ሰራተኞች ናቸው።

የትምህርት ሚነስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ የሚኒስቴር  መስሪያ ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞችን በማስተባበር በተሰበሰበ ገንዘብ ድጋፉ መደረጉን ገልጸዋል።

ድጋፉ በቀጣይነትም ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

በሚኒስቴሩ በኩል የሚደረገው በጎ ተግባር እንዳለ ሆኖ በተያዘው ዓመት የትምህርት ዘርፉ የ500 ሚሊየን ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በይፋ እንደሚጀመርም ገልፀዋል።

በአራዳ ክፍለ የወረዳ ዘጠኝ ዋና ስራአሰፈፃሚ አቶ ታሪኩ  እረታ የትምህርት ሚኒስቴር ላደረገው ድጋፍ አመስግነዋል።

Related posts

Leave a Comment