የኮሮናቫይረስ በሽታ ወረርሽኝ መሆኑ ታወጀ

መጋቢት 2/2012 (ኢዘአ) የዓለም ጤና ድርጅት ዓለምን እያስጨነቀ ያለው የኮሮና ቫይረስ በሽታ “ወረርሽኝ” መሆኑን ዛሬ ምሽት አውጇል። ባለፉት ሁለት ሳምንታት ከቻይና ውጪ በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በ13 እጥፍ መጨመሩን የዓለም ጤና ድርጅት ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም መግለጻቸውን ነው ቢቢሲ የዘገበው። በሽታውን በተመለከተ እርምጃ ለመውሰድ የታየው ቸልተኝነት “በጣም እንዳሳሰባቸው” የተናገሩት ዶክተር ቴዎድሮስ ፤ በሽታው ወረርሽኝ ተብሎ […]

Read More

በጉጂ ዞን ለ43 የፈጠራ ባለቤቶች እውቅናና የምስክር ወረቀት ተሰጠ

ነገሌ (ኢዜአ ) መጋቢት 2/2012፡- በኦሮሚያ ጉጂ ዞን በፈጠራ ስራ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ላበረከቱ የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆች ተማሪዎችና መምህራን ዛሬ በነገሌ ከተማ እውቅናና የምስክር ወረቀት ተሰጠ፡፡ አዳዲስ የፈጠራ ስራዎችን በማቅረብ ልማትን ለመደገፍ የድርሻቸውን እንደሚወጡ እውቅና ያገኙ ተማሪዎችና መምህራን ገልጸዋል፡፡ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ከኑ ቦሩ በፈጠራ ስራ አዳዲስ ቴክኖሎጂዎቹን ላበረከቱት 43 ተማሪዎችና መምህራን እውቅናና የምስክር ወረቀቱን […]

Read More

የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚቻል መረዳታቸውን የብልጽግና ፓርቲ

አዲስ አበባ (ኢዜአ) መጋቢት 2/2012 የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ማጠናቀቅ እንደሚቻል መረዳታቸውን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ መካከለኛ አመራሮች ገለጹ።

አመራሮቹ በእንጦጦ ፓርክ ጉብኝት አድርገዋል። በጉብኝቱበየአካባቢያቸው የሚከወኑ የልማት ፕሮጀክቶች በጥራትና በፍጥነት ሊጠናቀቁ የሚችሉበትን ሁኔታ እንዳሳያቸው ገልጸዋል።

ከተለያዩ የኦሮሚያ ዞኖች የተው…

Read More

የከተማ ግብርናን የከተሜነት መገለጫ እንደሆነ የሚየያስተዋወቅ የሚያስተዋውቅ ኤግዚቢሽንና ባዛር ሊካሄድ ነው

 አዲስ አበባ (ኢዜአ) መጋቢት 2/2012 በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል የሚካሄደውን ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ግብርና እና መልሶ ማቋቋም ኮሚሽን የተዘጋጀ እንደሆነ ተገልጿል። በመጋቢት 3 ቀን 2012 ዓ.ም የሚከፈተው ኤግዚቢሽንና ባዛር “ምግባችን ከደጆቻችን” በሚል መሪ ሃሳብ እንደሚከበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የከተማ ግብርና እና መልሶ ማቋቋም ኮሚሽነር ወይዘሮ ፈትያ መሐመድ ተናግረዋል። ኮሚሽነሯ በሰጡት […]

Read More

በበርበሬ ምርት ላይ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎች ድርጅታቸው ታሸገ

ሰቆጣ (ኢዜአ ) መጋቢት 02/2012 ፡- በሰቆጣ ከተማ አስተዳደር አለአግባብ በበርበሬ ምርት ላይ የተጋነነ ዋጋ የጨመሩ ነጋዴዎች ድርጅታቸው አንዲታሸግ መደረጉን የከተማው ንግድና ገበያ ልማት ጽህፋት ቤት አስታወቀ።የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መላሽ ወርቃለማው ለኢዜአ እንደተናገሩት የታሸጉት ድርጅቶች በከተማው የበርበሬ ጀምላ አከፋፋይ  የሆኑ 11  ነጋዴዎች ናቸው። ነጋዴዎቹ ምንም ዓይነት የበርበሬ ምርት እጥረትም ሆነ የዋጋ ጭማሬ ሳይኖር እንዳለ […]

Read More

ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ ድጋፋቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ገለፁ

አዲስ አበባ  መጋቢት 2/2012 (ኢዜአ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሲያደርጉት የቆዩትን ሁለንተናዊ ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ የተለያዩ የሕብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ገለፁ። ከኢዜአ ጋር ቆይታ ያደረጉ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍል ተወካዮች ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ ግድቡን ስትገነባ በዚህ ወንዝ ልማትን የማከናወን ተፈጥሯዊ መብቷን በመጠቀም መሆኑን ተናግረዋል። የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ አሰሪዎች ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ታደለ ይመር እና አትሌት ደራርቱ ቱሉ፤ ፕሮጀክቱ ተጠናቆ ማየት […]

Read More

በልመና ከተሰማሩ ግለሰብ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ ተገኘ

አርባምንጭ መጋቢት 07/2012 ( ኢዜአ) በአርባ ምንጭ ከተማ በልመና ከተሰማሩ ግለሰብ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ገንዘብ ተገኘ።  ጉዳዩ እንዲህ ነው፤ ግለሰቡ በአርባምንጭ ከተማ ጉርባ ቀበሌ በአንድ የእምነት ተቋም  አቅራቢያ በልመና የሚተዳደሩ ናቸው። በበጎ ስራ የተሠማሩ ወጣቶች ዛሬ የግለሰቡን መጠለያ  በማደስ ላይ እንዳሉ  እያንዳንዳቸው 50 ኪሎ ግራም  የሚይዙ ሶስት  የተሞሉ ከረጢቶችን  ይመለከታሉ። ከረጢቶቹን ከተቀመጡበት ለማንሳት ሲሞክሩ  ከባድ በመሆናቸው ለጊዜው […]

Read More

”ነጋሪ” መጽሔት አነጋጋሪ አገራዊ ጉዳዮች ያተኮሩ ጽሁፎችን ይዛ ወጥታለች

 አዲስ አበባ (ኢዜአ) መጋቢት 2/2012 በኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት (ኢዜአ) የምትዘጋጀው ”ነጋሪ” መጽሔት አነጋጋሪ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ርዕሰ ጉዳዮችን ይዛ ወጥታለች። መጽሔቷ በአራተኛ ዓመት ቁጥር 11 ዕትሟ ከያዘቻቸው ጉዳዮች መካከል በጥላቻ ንግግርና የሐሰት ማስረጃ፣ ሲቪል ሰርቪስ፣ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥና የቱሪዝም ልማት ዓበይት ጉዳዮች ናቸው። ”በሩ ገርበብ ይበል!” የሚል የሽፋን ርዕስ ያገኘው ጉዳይ በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በጸደቀው የጥላቻ ንግግርና የሃሰተኛ መረጃ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው ዓዋጅ የፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ […]

Read More