የተለያዩ ተቋማት ለኮሮና ስርጭት መከላከያ 16 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ

የአገር መከላከያ ደጀን እግረኛ ጦርን ጨምሮ ስምንት ተቋማት ለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭት መከላከል ስራ የሚውል የ16 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ለብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረከቡ።  የተቋማቱ ድጋፉን በሰላም ሚኒስቴር በመገኘት የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ለተቋቋመው ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ የሃብት አሰባሰብ ንዑስ ኮሚቴ  አስረክበዋል። በድጋፉ ከተሳተፉት የደጀን እግረኛ ክፍለ-ጦር፣ ዴማዴስ የጽዳት ማምረቻ ድርጅት፣ ስቲል RMI እና ግሩፕ ካምፓኒ፣ አልሀበሻ ሬስቶራንት፣ የህዳሴ ቴሌኮም እና አያት ሼር ኩባንያ ይገኙበታል። ተቋማቱ ወደፊትም ተሳትፏቸው እንደሚቀጥል […]

Read More

ቻይና በኢትዮጵያ ያለውን የኮሮናቫይረስ ስርጭት ለመከላከል የባለሙያና የቁሳቁስ ድጋፍ አደረገች

ሚያዚያ 8 / 2012  (ኢዜአ)  በኢትዮጵያ እየተደረገ ባለው የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ የመከላከል ስራ ላይ የሚሰማራ 12 አባላትን የያዘ የህክምና ቡድንና በርካታ ቁሳቁሶች በዛሬው ዕለት ከቻይና አዲስ አበባ ገብቷል። ቡድኑ የጸረ-ወረርሽኝ ህክምና ባለሙያዎች ያሉት ሲሆን ”በተባበረ ክንድ እናሸንፋለን” በሚል መሪ ሃሳብ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ለኢትዮጵያ ድጋፍ ለማድረግ ከቻይና የመጣ ነው። የሕክምና ቡድኑ ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር […]

Read More

ንግድ ባንክ የሆቴልና መሰል አገልግሎት ደንበኞቹ ያቀረቡለትን የብድር እፎይታ ጥያቄ ለመመለስ ጥናት እያደረገ ነው

ሚያዚያ 8 / 2012  (ኢዜአ)  የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሆቴልና መሰል አገልግሎት ዘርፍ ደንበኞቹ ያቀረቡለትን ‘የብድር እፎይታ ጊዜ ይሰጠን’ ጥያቄ ለመመለስ ጥናት እያደረገ መሆኑን ገለጸ። በሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ለተሰማሩት ደንበኞቹ ደግሞ የወረርሽኙ የወደፊት ሁኔታ ታይቶ የሚወሰን ይሆናል ። የዓለምን ምጣኔ ሃብታዊ እንቅስቃሴ በመግታት ሁለንተናዊ ቀውስ እያስከተለ ያለው ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ደካማ ኢኮኖሚ ላይ ‘በእንቅርት ላይ ጆሮ […]

Read More

በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚኖሩት ወይዘሮ እናኑ አሰምሬ የግል ሕንጻቸውን ለኮሮና መከላከል ተግባር እንዲውል ሰጡ

ሚያዚያ 8 / 2012  (ኢዜአ)  በቦሌ ክፍለ ከተማ የሚኖሩት ወይዘሮ እናኑ አሰምሬ በወር እስከ 200 ሺህ ብር የሚከራይ የግል ሕንጻቸውን ለኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) መከላከል ተግባር እንዲውል ሰጡ።  ለተለያዩ የቢሮ አገልግሎቶች ተከራይቶ እስከ 200 ሺህ ብር ወርሃዊ ገቢ የነበረውን ሕንጻ በዛሬው እለት ባለቤቷ ወይዘሮ እናኑ ለጤና ሚኒስቴር አስረክበዋል። ሕንፃውን የጤና ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ሰሃርላ አብዱላሂ በቦታው ተገኝተው […]

Read More

በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ በ83 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር የተገነባ የውሃ ፕሮጀክት ተመረቀ

አዲስ አበባ ሚያዚያ 8/2012(ኢዜአ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በለገጣፎ ለገዳዲ ከተማ አስተዳደር ወልጋዎ ቀበሌ ያስገነባውን የውሃ ፕሮጀክት አስመረቀ። ፕሮጀክቱ 83 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል። በምረቃ በስነ ስርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፤ የፕሮጀክቱ ሙሉ ወጪ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የተሸፈነ ነው። ፕሮጀክቱ በዋናነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና በአዲስ አበባ ዙሪያ ኦሮሚያ ልዩ ዞን መካከል […]

Read More

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትውልድ የጣለብንን ኃላፊነት ለመወጣት በትኩረት እንሰራለን ..የጤና ባለሙያዎች

ድሬዳዋ፣ሚያዚያ 8/2012 (ኢዜአ) የኮሮና ቫይረስ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል ሃገርና ትውልድ የጣለባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ገለጹ። በሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ህሙማንን ለማከም የተደረገው ዝግጅት በከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ዛሬ ተጎብኝቷል። የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ሲስተር መስከረም አሰፋ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና ህክምና አገልግሎት […]

Read More

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ትውልድ የጣለብንን ኃላፊነት ለመወጣት በትኩረት እንሰራለን ..የጤና ባለሙያዎች

ድሬዳዋ፣ሚያዚያ 8/2012 (ኢዜአ) የኮሮና ቫይረስ ሊያደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመከላከል ሃገርና ትውልድ የጣለባቸውን ኃላፊነት እንደሚወጡ በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር የሳቢያን ጠቅላላ ሆስፒታል የሚሰሩ የህክምና ባለሙያዎች ገለጹ። በሆስፒታሉ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከልና ህሙማንን ለማከም የተደረገው ዝግጅት በከተማ አስተዳደሩ የካቢኔ አባላት ዛሬ ተጎብኝቷል። የሆስፒታሉ ሥራ አስኪያጅ ሲስተር መስከረም አሰፋ በጉብኝቱ ላይ እንደተናገሩት፤ ሆስፒታሉ በሙሉ አቅሙ የኮሮና ቫይረስ መከላከልና ህክምና አገልግሎት […]

Read More

የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለተለያዩ በጎ አድራጊ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ፣ሚያዚያ 8/2012 (ኢዜአ) የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ለአምስት የተለያዩ በጎ አድራጊ ድርጅቶች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። የብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ኮሚሽነር ጀኔራል ደመላሽ ገብረሚካኤል ከሠራተኞች ወርሃዊ ደመወዝ ተዋጥቶ የተሰባሰበውን ገንዝብ በዛሬው እለት ለበጎ አድራጊ ድርጅቶቹ አስረክበዋል። የገንዘብ ድጋፍ ያደረገላቸው አምስት በጎ አድራጊ ድርጅቶች ሲሆኑ ለእያንዳንዳቸው 150 ሺህ ብር በድምሩ የ750 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል። ድጋፉ […]

Read More