በመሬት ናዳ ለተፈናቀሉ ወገኖች የቀለብና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገላቸው

አርባምንጭ ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ )በጋሞ ዞን ሶስት ወረዳዎች ሰሞኑን ተከስቶ በነበረ የመሬት ናዳ ለተፈናቀሉ ወገኖች የአንድ ቀለብና ቁሳቁስስ ድጋፍ መደረጉን የዞኑ አደጋ ስጋት ስራ አመራር ጽህፈት ቤት አስታወቀ።የጽህፈት ቤቱ  ኃላፊ አቶ ተስፋዬ ማርቆስ  ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት ድጋፍ የተደረገው ከቤት ንብረታቸው ለተፈናቀሉ 79 ሰዎች  ነው። ድጋፉም የዞኑ አስተዳደርና ከኢትዮጵያ ቀይመስቀል ማህበር ጎፋ ቅርንጫፍ ጋር በመሆን ለአንድ […]

Read More

በአዲስ አበባ በትራንስፖርት ዘርፍ የኮሮናቫይረስን በመከላከል በኩል የጥንቃቄ ጉድለት ይስተዋላል

አዲስ አበባ፤ሚያዝያ 13/2012(ኢዜአ) በአዲስ አበባ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በትራንስፖርት ዘርፍ የወጡ መመሪያዎች ተግበራዊ እየተደረጉ ቢሆንም አሁንም የጥንቃቄ ጉድለት መኖሩ ተገልጿል።የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ በትራንስፖርት ዘርፍ የወጡ መመሪያዎች ትግበራና የትራንስፖት እንቅስቃሴን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ዛሬ ምልከታ አድርጓል። በትራንስፖርት ውስጥ የሚፈጠር ንክኪን ለመቀነስ ታክሲና የብዙሃን ትራንስፖርት ቀደም ሲል ይጭኑት ከነበረው የተሳፋሪ ቁጥር በግማሽ እንዲቀንሱ መወሰኑ ይታወሳል። የጉብኝቱ ተሳታፊዎች […]

Read More

በደሴ ደም ልገሳ መሻሻል አሳይቷል

ደሴ ኢዜአ ሚያዚያ 13 ቀን 2012 የደሴ ደም ባንክ አገልግሎት ከኮሮና ቫይረስ መከሰት ጋር ተያይዞ አጋጥሞት የነበረው የደም እጥረት መሻሻል ማሳየቱን ተገለፀ።በደሴ ከተማ የሚገኘው “ከዳም” በጎ አድራጎት ማህበር አባላት ዛሬ ደም ለግሰዋል፡፡ የደሴ ደም ባንክ አገልግሎት ኃላፊ አቶ ታደሰ ሲሳይ እንደገለጹት በኮሮና ቫይረስ ስጋት ምክንያት የደም ለጋሾች ቁጥር በብዙ እጥፍ በመቀነሱ የደም እጥረት አጋጥሞ መቆየቱን […]

Read More

በግል ትምህርት ቤቶች ዙሪያ የተላለፈው ውሳኔ ሚዛናዊነቱ ታይቶ ነው- ትምህርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ሚያዚያ 13 /2012 በአዲስ አበባ በግል ትምህርት ቤቶች ዙሪያ የተላለፈው ውሳኔ ሁሉንም ባለደርሻ አካላት ያማከለና ሚዛናዊ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ።የትምህርት ሚኒስቴር በግል ትምህርት ቤቶች የተማሪዎች ወርሃዊ ክፍያና የመምህራን የአስተዳደር ሰራተኞች ደመወዝና ተያያዥ ጉዳዮች አስመልክቶ በተወሰኑ ውሳኔዎች ላይ ዛሬ መግለጫ ሰጥቷል። በኮሮና ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት ትምህርት ቤቶች ከመጋቢት 7 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ መዘጋታቸው የሚታወስ […]

Read More

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የጭነት አገልግሎት ፍላጎትን ለመመለስ እየሰራ ነው

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ መስፋፋት ያመጣውን የአየር መንገድ የጭነት አገልግሎት ፍላጎትን ለመመለስ እየሰራች እንደምትገኝ ተገለፀ ፡፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው በርካታ የጭነት አገልግሎትና የህክምና ቁሳቁስ በሚፈለጉበት ቦታ ማድረስን የመሳሰሉ አስፈላጊ የጭነት ፍሰት የማመቻቸት ስራ እንደሚሰራም አስታውቋል፡፡ በአፍሪካ በትልቁ የትራንስፖርት ጭነት ተርሚናል ስር ያለው ዘመናዊው የኢትዮጵያ የጭነት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት […]

Read More

ለኮድ ሁለት መኪኖች የወጣው ፈረቃ የሕዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዎችንና የአምቡላንሶችን ምልልስ ለማፍጠን የታሰበ ነው-ባለስልጣኑ

አዲስ አበባ ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ) ኮድ ሁለት መኪኖች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ መደረጉ የኮቪድ – 19 ስርጭትን ከመከላከል ጎን ለጎን የሕዝብ ማመላለሻና የአምቡላንስ ተሽከርካሪዎችን ምልልስ ለማፋጠን መሆኑን የትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ። በአሁኑ ወቅት መንግስት የሚያወጣቸው መምሪያዎች ሕዝቡን ከአደጋ ለመታደግ መሆኑ ታውቆ ለተፈጻሚነቱ ተባባሪ መሆን እንዳለበትም ተገልጿል።የኢትዮጵያ መንግስት የኮቪድ-19ን ስርጭት ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፉ የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑ ይታወቃል። ባለፈው […]

Read More

በአፋር ክልል የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ተጠየቀ

ሰመራ (ኢዜአ) ሚያዚያ 13 / 2012 በአፋር ክልል የኮሮና ቨይረስ ለመከላከል በአዋሳኝ አካባቢዎች በሚደረገው ቁጥጥር የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ተጠየቀ፡፡ የአፋር ክልል ከጅቡቲና ከኤርትራ ጋር የሚዋሰን በመሆኑ በርካታ ሰዎች ድንበር አቋርጠው ወደ ክልሉ የሚገቡበትና የሚወጡበት አጋጣሚ በርካታ ነው ። ወደ ክልሉ የሚደረገውን የሰዎች ፍሰት ከኮሮና ቫይረስ ስርጭት ጋር ተያይዞ ችግር እንዳይፈጠር በኤሌደአር ወረዳ በጋላፊና በበልሆ […]

Read More

እንግሊዝ ለዚምባቡዌ 43.6 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገች

ሚያዝያ 13/2012 (ኢዜአ)  የእንግሊዝ መንግሥት 43.6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የኮሮና መከላከያ የህክምና አቅርቦት ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

በዚምባቡዌ የእንግሊዝ
አምባሳደር የሆኑት ሜላኒ ሮቢንሰን፣ ዚምባቡዌ ኮቪዲ19ን  ለመከላከል በምታደርገው እንቅስቃሴ ትልቅ አጋር በመሆን 44
ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ድጋፍ የአገራቸው መንግስት ማድረጉን ገልጸዋል፡፡

ይህም የእንግሊዝና…

Read More