የጤና ሚኒስቴር የቴንሴንት ፋውንዴሽን የላካቸውን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶች ተረከበ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 13/2012( ኢዜአ) የጤና ሚኒስቴር የቴንሴንት ፋውንዴሽን የላካቸውን የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ ቁሳቁሶች ተረከበ። የቴንሴንት ኩባንያ የታዋቂው ማኅበራዊ ትስስር ገጽ “ዊ ቻት” ባለቤት ሲሆን በዋናነት በቴክኖሎጂ ዘርፍ  የተሰማራ ኩባንያ ነው። የኩባንያው ፋውንዴሽን ለኢትዮጵያ 100 ሺህ የመመርመሪያ መሳሪያዎችና ሁለት ሚሊዮን የህክምና  ጓንቶችን የላከ ሲሆን፤ ድጋፉን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ታደሰ ቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ […]

Read More

ግብጽ የአስዋንን ግድብ ስትገነባ የኢትዮጵያን ፈቃድ አልጠየቀችም – የመብቶች ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን

አዲስ አበባ   ግንቦት  13/2012 (ኢዜአ) “ግብጽ የአስዋንን ግድብ ስትገነባ የኢትዮጵያን ፈቃድ አልጠየቀችም” ሲል ጥቁር አሜሪካዊው የመብቶች ተሟጋች ጄሲ ጃክሰን አስታወቁ። ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድቡን አስመልክቶ የምታከናውናቸው ስራዎች ዓለም አቀፍ የውሃ ህጎችን የተከተለ ነውም ብለዋል። የሲቪክ መብቶች ተቋም “ሬንቦው ፑሽ ኮሊሽን” መስራች ጄሲ ጃክሰን ለጥቁር የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ኮሚቴ ሊቀመንበር ሚስ ካረን ባስ በጻፉት አራት ገጽ ደብዳቤ ላይ […]

Read More

‘ትውልድን በትምህርት የመገንባት ስራ ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ነው – ኢንጂነር ታከለ ኡማ

አዲስ አበባ   ግንቦት  13/2012 (ኢዜአ) ትውልድን በትምህርት የመገንባት ስራ ከምንም በላይ ቅድሚያ የምንሰጠው ተግባር ነው ሲሉ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ ገለጹ። የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ በእጅጉ ከተጎዱ ዘርፎች መካከል ትምህርት አንዱ ነው። እንደተቀረው ዓለም ሁሉ በኢትዮጵያም ቫይረሱ ተገኘ ከተባለበት ጊዜ አንስቶ ከከፍተኛ የትምህርት ተቋም እስከ መጀመሪያ ደረጃ ያሉ ተማሪዎች ትምህርት አቋርጠው በቤታቸው ተቀምጠዋል። […]

Read More

በደቡብ ክልል ወረርሽኙን ለመከላከል የገንዘብና የዓይነት ድጋፍ ላደረጉ አካላት እውቅና ተሰጠ

ሐዋሳ፣ ግንቦት 13/2012( ኢዜአ) በደቡብ ክልል የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እየተደረገ ባለው ጥረት ላቅ ያለ የገንዘብና ዓይነት ድጋፍ ላደረጉ ድርጅቶችና ተቋማት እውቅና ተሰጠ። የክልሉ ኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል  ዛሬ ባዘጋጀው  ስነስርዓት እውቅና የተሰጠው በግንባታ፣ንግድ፣ ባንክና ሌሎችም መስኮች ለተሰማሩ  ነው። የግብረ ኃይል ሰብሳቢና የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ርስቱ ይርዳው እንዳሉት ድጋፉ ለወገን ደራሽ ወገን ነው የተባለው በተግባር […]

Read More

ኮሌጁ ለመልሶ መጠቀም ያዘጋጃቸውን ዘመናዊ የዳቦ ማከፋፈያና መሻጫ አውቶቡሶች አስረከበ

አዲስ አበባ   ግንቦት  13/2012 (ኢዜአ) የአቃቂ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ በዘመናዊ መንገድ ለመልሶ መጠቀም ያዘጋጃቸውን 53 የዳቦ ማከፋፈያና መሸጫ አውቶቡሶች ለአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ አስረከበ። የዳቦ ማከፋፈያና መሻጫ  አውቶቡሶቹ በቅርቡ ስራ የሚጀምረውን የሸገር ዳቦ ፋብሪካ ምርቶች ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ያግዛሉ ተብሏል። በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የመንግስት አገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ አገልግሎታቸውን የጨረሱ አውቶቡሶችን በጥራት በማደስ ለአገልግሎት ለማብቃት የተሰራውን ስራ አድንቀዋል። ይህ የኮሌጁ ተግባር ሌሎችን የሚያስተምር እንደሆነም ገልጸዋል። በመዲናዋ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት ያቆሙ 400 አውቶቡሶችን በዘመናዊ መንገድ በማደስ ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ እንደሚገባም ጠቁመዋል። ኮሌጁ የከተማ ግብርናን የማስፋፋትና ሌሎችም ስራዎቹ ውጤታማ እንዲሆኑ የከተማ አስተዳደሩ ድጋፍ እንደሚያደርግም አስታውቀዋል። ኮሌጆች ዋነኛ ተግባራቸው የፈጠራ ስራ፣ ቴክኖሎጂ ማላመድና የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራት በመሆኑ በዚሁ ላይ ማተኮር እንዳለባቸውም አሳስበዋል። የኮሌጁ ዲን አቶ ደመላሽ ተስፋዬ ኮሌጁ  በዘመናዊ መንገድ ጠግኖ ለአገልግሎት ያዘጋጃቸው 53 አውቶቡሶች  በ53 ኢንተርፕራይዞች ለሚገኙ 265 ዜጎች የስራ ዕድል እንደሚፈጥሩ ገልጸዋል። በተጨማሪም ኮሌጁ ኮቪድ-19ን መከላከል የሚያስችሉና ከእጅ ንክኪ ነፃ የሆኑ ማስታጠቢያዎች እንዲሁም የአፍና አፍንጫ መሸፈኛዎችን በመስራት ሃላፊነቱን እየተወጣ መሆኑንም እንዲሁ። […]

Read More

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከላከል ላይ በማተኮር ለተዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር የዕውቅና ፕሮግራም እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝ መከላከል ላይ በማተኮር ለተዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር የዕውቅና ፕሮግራም ዛሬ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። በመድረኩ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር አብርሃም በላይን ጨምሮ የተጠሪ ተቋማት ኃላፊዎች፣ ተጋባዥ  እንግዶችና የፈጠራ ባለሙያዎች ተገኝተዋል። ወረርሽኙን ለመግታትና ለመከላከል አዳዲስ ምርምሮችን ማካሄድና የወጣቶችን መነሳሳት በተደራጀ አግባብ ለመምራት ውድድሩ መዘጋጀቱ […]

Read More

በቴሌኮም ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች ከዛሬ ጀምሮ ፍላጎታቸውን እንዲያሳውቁ ተጠየቀ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 13/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን በቴሌኮም ዘርፍ የመሰማራት ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች ከዛሬ ጀምሮ ፍላጎታቸውን የሚያሳውቁበት ሰነድ ይፋ ማድረጉን አስታወቀ። መንግስት የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝን ከመከላከል ጎን ለጎን አገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን አጠናክሮ መቀጠሉን ገንዘብ ሚኒስቴር ገልጿል። የኢትዮጵያ ኮሙኒኬሽን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ባልቻ ሬባ ለኢዜአ እንዳሉት፤ ባለስልጣኑ ሁለት የቴሌኮም ፈቃዶችን ለመስጠት […]

Read More

የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ   ግንቦት  13/2012 (ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ እና ከፍተኛ የልዑካን ቡድናቸው፣  ከሱዳኑ አቻቸው አብደላ ሐምዶክ ጋር በኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ዙሪይ ተወያዩ። በቪድዮ ኮንፍረንስ ባደረጉት ውይይት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን አስመልክቶ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያልተቋጩ ጉዳዮችን ለማጠናቀቅ እና የተዛቡ ግንዛቤ ዎችን  ማጥራትን ያለመ ነው ተብሏል። በዋናነትም የአካባቢ ጥበቃ፣ የግድቡ የደኅንነት ሁኔታ እና የመረጃ ልውውጥን ስለ […]

Read More

የሐማሬሳ የምግብ ዘይት አክሲዮን ማህበር የዱቄትና ዘይት ድጋፍ አደረገ

ሐረር ፣ ግንቦት 13/ 2012 (ኢዜአ) በሐረር ከተማ የሚገኘው የሐማሬሳ የምግብ ዘይት አክሲዮን ማህበር ከግማሽ ሚሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የምግብ ዱቄትና ዘይት በክልሉ ለተቋቋመው ገቢ ማሰባሰብና ሀብት ማፈላለግ አብይ ኮሚቴ አስረከበ። የምግብ ዱቄቱንና ዘይቱን ያስረከቡት የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ገዛኸኝ ድጋፌ “የፍቅር ማዕድ” በሚል ስያሜ የተደረገው ድጋፍ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ለችግር ለተጋለጡ […]

Read More