በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ለይቶ ማቆያ ለሚያገለግሉ ሠራተኞች የበዓል ስጦታ ተበረከተ

አዲስ አበባ፣ግንቦት 14/2012(ኢዜአ) የለይቶ ማቆያ ኳራንቲን ቦታዎች ንኡስ ኮሚቴ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ በተዘጋጀ የለይቶ ማቆያ ቦታ የተለያዩ አገልግሎት ለሚሰጡ ሠራተኞች የበዓል ስጦታ አበረከተ። የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ህግና የንኡስ ኮሚቴው ሰብሳቢ ወይዘሮ አዳነች አበቤና የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ሚኒስትሯ ወይዘሮ ፈይሰል አብዱላሂ ዛሬ በቦታው ተገኝተው ሠራተኞቹን አመስግነዋል። ንኡስ ኮሚቴው በዚህ ወቅት ስምንት በግና ፍየሎችን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት […]

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ ለእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14/2012(ኢዜአ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓል አስመልክተው ለእስልምና እምነት ተከታዮች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው የረመዳን ወር ሥጋዊ ፍላጎትን በመንፈሳዊ ጽናት መርታትንና ራስን ማስገዛትን የመማሪያ ወር መሆኑን አስታውሰዋል። ሰው ከምድራዊ ሕይወቱ ባሻገር ያለውን ሰማያዊ ዓለም በጥቂቱ የሚቀምስበት ወቅት እንደሆነም ነው የገለጹት። “ብዙዎች ረመዳን […]

Read More

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ሊየጋጥም የሚችለውን ምርት ለማካካስ እየተሰራ ነው … ግብርና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2012( ኢዜአ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በ2012/13 ምርት ዘመን ሊያጋጥም የሚችለውን ምርት ለማካካስ እየተሰራ መሆኑን የግብርና ሚኒስትር ዴኤታ አስታወቁ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ተጽዕኖ ከሚያሳድርባቸው መስኮች አንዱ የግብርናው ዘርፍ ነው። ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ሳኒ ረዲ ለኢዜአ እንደገለጹት በወረርሽኙ ምክንያት ሊገጥም የሚችለውን እጥረት ለመከላከል የተለያዩ አቅጣጫዎች ተቀምጠዋል። ባለፈው የምርት ዘመን  በዋና ዋና የአዝርዕት ሰብሎች […]

Read More

በደቡብ ክልል በወረርሽኙ ምክንያት የተፈጠረውን ጫና ለመቀነስ የታክስ ዕዳ ማቅለያ ተደረገ

ሐዋሳ ፣ ግንቦት 14/2012 (ኢዜአ)  በደቡብ ክልል በኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ኢኮኖሚው ያጋጠመውን ጫና ለመቀነስ ግብር ከፋዮች የታክስ ዕዳ ማቅለያ እንደተደረገላቸው የክልሉ ገቢዎች ባለሥልጣን አስታወቀ።  የዕዳ ማቅለያ ውሳኔውን አስመልክቶ የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ዘይቱና ኢብራሂም ለጋዜጠኞች መግለጫ ሰጥተዋል። የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወይዘሮ ዘይቱና ኢብራሂም እንዳሉት ወረርሽኙ በክልሉ ኢኮኖሚ ላይ እያስከተለ ያለውን አደጋ እንዲሁም የተከማቸ የግብርና የታክስ […]

Read More

ህዝበ ሙስሊሙ በዓሉን ኮሮናን በመከላከል በጥንቃቄ ማክበር አለበት ….. የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር

ሀዋሳ፣ ግንቦት 14/2012 (ኢዜአ) ህዝበ ሙስሊሙ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል መንግስት ያወጣውን መመሪያ ተግባራዊ በማድረግ በጾም ወቅት በቤቱ ጸሎት ሲያደርግ እንደቆየው ሁሉ በዓሉንም በጥንቃቄ ማክበር እንደሚገባ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ። የከተማዋ አስተዳደር ከሲዳማ ዞን እስልምና ምክር ቤት ጋር በመተባበር 250 ደጋፊ የሌላቸው የእስልምና ተከታዮች ለበዓሉና ለአንድ ወር ምግብ የሚሆን የምግብና የንጽህና መጠበቂያ ድጋፍ አድርጓል። የሀዋሳ […]

Read More

በአዲስ አበባ ከተማ ለ300 ግለሰቦች ለኢድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ በጎች ተበረከቱ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 14/2012 (ኢዜአ) በአዲስ አበባ ከተማ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ለ300 ግለሰቦች ለኢድ አልፈጥር በዓል ማክበሪያ በጎች ተበረከቱ።  በክፍለ ከተማው አቅም ለሌላቸው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች የተበረከቱት በጎች ከ880ሺህ ብር በላይ ወጪ እንደተደረገባቸው ዛሬ በተካሄደው የርክክብ ሥነ ሥርዓት ተገልጿል። የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ አደም ኑሪ የክፍለ ከተማውን የንግድ ማህበረሰብና ግለሰቦች በማስተባበር የእምነቱ ተከታዮች […]

Read More

በአዳማ ከተማ ከ730 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድ እቃዎች የተገኘባቸው አሽከርካሪዎች ተያዙ

አዳማ፣ ግንቦት 14/2012 (ኢዜአ ) በአዳማ ከተማ ከ730 ሺህ ብር በላይ የሚገመቱ የኮንትሮባንድና ህገ ወጥ እቃዎች ሲያጓጉዙ የተገኙ ስድስት አሽከርካሪዎች መያዛቸውን ፖሊስ አስታወቀ። የከተማዋ አስተዳደር  ፖሊስ መምሪያ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ረዳት ኢንስፔክተር ወርቅነሸ ገልሜሳ ዛሬ ለኢዜአ እንደገለጹት በግለሰቦቹ ተሽከርካሪዎች ትናንት ሲጓጓዙ ከነበሩት  መካከል  ልባሽ ጨርቆች፣ ሲጋራ፣ ሺሻ እና የኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ይገኙበታል። የከተማዋ የፖሊስ አባላት ህገ […]

Read More

ወደ ባህረ ሰላጤው አገራት ለስደት የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን የጉዳቱን ልክ በደንብ እንደማያውቁ ተገለጸ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 14/2012(ኢዜአ) ለሥራ ፍለጋ ወደ ባህረ ሰላጤው አገራት ለስደት የሚጓዙ ኢትዮጵያዊያን የጉዳቱን ልክ በደንብ እንደማያውቁ አንድ ጥናት አመለከተ። በዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅትና በአውሮፓ ህብረት የሚተገበረው የአፍሪካ ቀንድ የጋራ የስደተኞች ጥበቃ መልሶ ማገናኘት ፕሮግራም ትብብር ‘ዘ ዲዛየር ቱ ትሪቭ ሪጋርድለስ ኦፍ ሪስክ’  በሚል ርዕስ ባካሄደው ጥናት ነው ጉዳዩን ይፋ ያደረገው። በጥናቱ እንደተገለጸው በምስራቅ የአገሪቱ […]

Read More

በዓሉ ኮሮናን በመከላከልና የተቸገሩትን በመርዳት ሊከበር ይገባል …. የአፋር ክልል ርእሰ መስተዳድር

ሰመራ፣ ግንቦት 14/2012 (ኢዜአ) ህዝበ ሙስሊሙ 1ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል ሲያከብር እራሱን ከኮሮና ቫይረስ ለመከላከል የበለጠ ተዘጋጅቶና አቅመ ደካሞችን በመደገፍ መሆን እንደሚገባው የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ አሳሰቡ ። የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባ ለህዝበ ሙስሊሙ እንኳን ለ1ሺህ  441ኛው ሂጅራ የኢድ አል-ፈጥር በአል አደረሳችሁ የሚል መልእክት አስተላልፈዋል። ርእሰ-መስተዳድሩ በአሉን አስመልክተው […]

Read More