ሕዝቡ የተጠራው ሰልፍ ለኮሮናቫይረስ እንደሚያጋልጠው አውቆ ቅድሚያ ለጤንነቱ ሊሰጥ ይገባል- የኦሮሚያ ክልል መንግስት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) የኦሮሚያ ክልል መንግስት ሕዝቡ በአንዳንድ ሃይሎች እየተጠራ ያለው የተቃውሞ ሰልፍ ለኮሮናቫይረስ  እንደሚያጋልጠው አውቆ ቅድሚያ ለጤንነቱ ሊሰጥና ጥያቄውን በትክክለኛ መንገድ ሊያቀርብ እንደሚገባ አሳስቧል። የክልሉ መንግስት በአጭር ጊዜ ውስጥ ስምንት የኮሮናቫይረስ መመርመሪያ ቦታዎችን ወደ ስራ ለማስገባት እየሰራ መሆኑንም ገልጿል።  የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በኮሮናቫይረስ መከላከልና ሰሞኑን በክልሉ በተለያዩ አካላት እየተጠሩ ያሉ ሰላማዊ ሰልፎችን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል። መግለጫውን የሰጡት በምክትል […]

Read More

የህወሃት አኩራፊዎች የግል ፍላጎታቸውን ለማስቀጠል ያልተቋረጠ ሴራ ይጎነጉናሉ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) የህዝባዊ ወያኔ ሃርነት ትግራይ (ህወሃት) አኩራፊዎች የግል ፍላጎታቸውን ለማስቀጠል ያልተቋረጠ ሴራ እየጎነጎኑ እንደሚገኙ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ አመለከተ።  ፓርቲው ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ የህወሓት የጥገኛ ገዢ መደብና ከተለያዩ የመንግስት መዋቅሮች የተሰባሰቡ የኩርፍያ አድመኞች በኢትዮጵያ ህዝብ ጫንቃ ላይ የመቆየት ፍላጎት ነበራቸው። ስብስቦቹ በቀድሞ የኢህአዴግ አወቃቀር በተለያዩ ግዜያት በተደረጉ ግምገማዎች የስርዓትና የሃገር አደጋዎችን በመለየት ለማስወገድ በተዘጋጁ መድረኮች ሲናዘዙና […]

Read More