የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትሔን ማበጀት ላይ ያተኮረ ውይይት ተካሄደ

ሰኔ 19/2012(ኢዜአ) የአፍሪካ ህብረት ዓባላት ቢሮ፣ ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ ለታላቁ የሕዳሴ ግድብ ከአፍሪካ የመነጨ መፍትሔን ማበጀት ላይ ያተኮረ ውይይት ማካሄዳቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታወቁ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት ፅሁፍ ውይይቱ ውጤታማ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ እንዲሁም ይህን አህጉራዊ ጠቀሜታ ያለው የከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ላስተባበሩት የአፍሪካ ህብረት ሰብሳቢ ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ እና ለህብረቱ […]

Read More

ህወሃት በወልቃይትና ራያ የአማራ ታሪካዊ ግዛቶች ላይ ሊያደርግ ያሰበዉ ምርጫ ተቀባይነት የለውም …አብን

ሰኔ 19 /2012 የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የህወሃት ሕገ ወጥ ቡድን በወልቃይትና ራያ የአማራ ታሪካዊ ግዛቶች ላይ ሊያደርግ ያሰበዉ ምርጫ ተቀባይነት የለውም አለ። ፓርቲው ዛሬ ያወጣው መግለጫ እንደሚከተለው ቀርቧል፤ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የሕወኃት ሕገ ወጥ ቡድን በወልቃይትና ራያ የአማራ ታሪካዊ ግዛቶች ላይ ሊያደርግ ያሰበዉ ምርጫ ተቀባይነት እንደሌለዉ ይገልፃል! የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ(አብን) የኢፌዲሪ ሕገ መንግስትን በተመለከተ የሚያራምደዉን […]

Read More

የአማራ ክልል የወጣት አደረጃጀቶች ለህዳሴው ግድብ ግንባታ የግማሽ ቢሊዮን ብር የቦንድ ግዥ ማከናወን ጀመሩ

ባህርዳር፣ ሰኔ 19/2012 ( ኢዜአ) በአማራ ክልል የሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች አስተባባሪነት ለህዳሴው ግድብ ግንባታ በሶስት ወራት ውስጥ ግማሽ ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ የሚያስችል የቦንድ ግዥ ዘመቻ ዛሬ ተጀመረ።

የቦንድ ግዥው የሚከናወነው አባይን እንገድባለን፣ ጣናን ከእምቦጭ እንታደጋለን በሚል መሪ ሃሳብ ነው።

በቦንድ ግዥው ማስጀመሪያ መርሃ ግብር&…

Read More

በሃዲያ ዞን በ464 ሚሊዮን ብር ወጪ አደጋ የመከላከል ስራ ተከናወነ

ሆሳዕና ሰኔ 19/2012 (ኢዜአ)  በሀድያ ዞን የተፈጥሮ አደጋ ለመከላከልና ተፈናቃይ ወገኖችን ለመታደግ በ464 ሚሊዮን ብር ወጪ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን የዞኑ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ገለፀ። በጽህፈት ቤቱ የቅድመ ማስጠንቀቂያ የስራ ሂደት ባለቤት አቶ በቀለ ጡሜቦ ለኢዜአ እንደገለጹት በዚህ ዓመት 78 የገጠር ቀበሌዎች ላይ በደረሰ የጎርፍ አደጋ በ9 ሺህ ሔክታር መሬት  ላይ የነበረ ቋሚና ጊዜያዊ ሰብል ወድሟል። በዚህም ከ84 ሺህ በላይ የህብረተሰብ ክፍሎች በመፈናቀል […]

Read More

የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን ለመደገፍ ዝግጁ ነው–ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር

ባህር ዳር፣ ሰኔ 19/2012( ኢዜአ ) የወጣቶች የክረምት ወቅት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ውጤታማ እንዲሆን አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆናቸውን የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች ጉዳይ ሚኒስትር ወይዘሮ ፍልሰን አብዱላሂ ገለጹ። በአማራ ክልል የበጀት ዓመቱ በጋ ወቅት የወጣቶች በጎ ፈቃድ አገልግሎት መዝጊያና የክረምቱ ማስጀመሪያ መረሃ ግብር ዛሬ በባህር ዳር ከተማ ተካሂዷል። በመረሃ ግብሩ ስነስርዓት ወቅት የተገኙት ሚኒስትሯ እንዳሉት […]

Read More

ሽምግልናና ድርድር ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችና ህጻናት ፍትህ እንዳያገኙ እያደረገ ነው –

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19/2012 ( ኢዜአ)  ሽምግልናና ድርድር ጾታዊ ጥቃት የሚደርስባቸው ሴቶችና ህጻናት ፍትህ እንዳያገኙ እያደረገ ነው ሲል ዝም አልልም ማህበረሰባዊ እንቅስቃሴ አስታወቀ። የፍትሕ አካላት ለጉዳዩ ተገቢውን ትኩረት አልሰጡትም ብሏል። የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ተከትሎ ሰዎች በቤታቸው እንዲቆዩ መንግሥት ካሳለፈው ውሳኔ በኋላ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚደርሱ ጾታዊና አካላዊ ጥቃቶች በአሳሳቢ ሁኔታ ጨምረዋል። ዋልታ ቴሌቪዥን ግንቦት 25 ቀን […]

Read More

የአፋርና አማራ ህዝቦች ሰላምና ደህንነትን በመጠበቅ ለልማት ስራዎች ትኩረት ይሰጣል

ደሴ  ሰኔ 19/2012 (ኢዜአ) የአፋርና አማራ ህዝቦች ሰላምና ደህንነትን በመጠበቅ የጋራ የልማት ስራዎችን ለማረጋገጥ በልዩ ትኩረት እንደሚሰራ የሁለቱ ክልሎች የሰላምና ደህንንት ቢሮዎች አስታወቁ፡፡ የአፋር ክልል ሰላምና ደህንነት ቢሮ ኃላፊ አቶ አህመድ መሃመድ ለኢዜአ እንደገለጹት የአፋር ክልል ከሦስት ክልሎች ጋር የሚዋሰን ቢሆንም በሰፊው የሚዋሰነው ከአማራ ክልል ጋር ነው። በዚህም የሁለቱ ክልል ህዝብ በፖለቲካ፣ በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ ልማትና […]

Read More

በህጻናትና ሴቶች ላይ የሚፈጸም ጥቃት በቃ ሊባል ይገባል -ጠቅላይ አቃቤ ህግ

ሰኔ 19 /2012 (ኢዜአ) በህጻናትና ሴቶች ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን በቃ ሊባል ይገባል ሲል የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ጥሪውን አቀረበ። ጠቅላይ አቃቤ ህጉ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው በዓለማችን ብሎም በአገራችን የኮሮና ቫይረስ ተግዳሮት እየተፈታተነን ባለበት ወቅት በህጻናትና በሴቶች ላይ የሚደርሰው ጥቃት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል። ይህን ችግር ለመቅረፍ የሁላችንም ኃላፊነት ነው ያለው መግለጫው፤ በተለይ የህግና የፍትህ […]

Read More

ኪነ-ጥበብ አገር በችግርና ፈተና ውስጥ ስትሆን ብርሃንና ተስፋን የማሳየት ኃላፊነቷን ልትወጣ ይገባታል

አዲስ አበባ ሰኔ 19/2012(ኢዜአ) ኪነ-ጥበብ አገር በችግርና ፈተና ውስጥ ስትሆን ብርሃንና ተስፋን የማሳየት ኃላፊነቷን መወጣት እንደሚገባት ተገለጸ።  ኢትዮጵያ በኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ወረርሽኝና እያስከተለ ያለው ጉዳት፣ የፖለቲካ አለመግባባቶች፣ ብሔርን መሠረት ያደረጉ ግጭቶች፣ የጸጥታ ሁኔታ፣ ሌሎች ችግሮችና ፈተናዎች ከፊቷ ተጋርጠውባታል። አሁን ያሉትን ፈተናዎች ለመሻገር ኪነ-ጥበብ ምን አይነት ሚና ሊኖራት ይገባል? በሚል ኢዜአ የኪነ- ጥበብ ባለሙያዎችን አነጋግሯል። ድምጻዊ ፀደኒያ […]

Read More

የ10 ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ለሕዝብ ውይይት ሊቀርብ ነው

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19/2012 ( ኢዜአ) የኢትዮጵያ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ መነሻ ሰነድ ለሕዝብ ውይይት እንደሚቀርብ የፕላንና ልማት ኮሚሽን አስታወቀ። ኮሚሽኑ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው የመነሻ ሰነዱ ውይይት ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ለ11 ቀናት ይካሄዳል። የውይይቱ ዓላማ የተለያዩ ባለድርሻ አካላትን በዕቅድ ዝግጅቱ እንዲሳተፉ ማስቻል፣ ከኅብረተሰቡ በሚገኝ ግብዓት ዕቅዱን ማዳበርና ግልጽ ባልሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ መስጠት መሆኑን […]

Read More