አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ዘገበ።

ዶይቸ ቬለ የአማርኛ ክፍል ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት ይህን ዘግቧል፦ አቶ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ በፌድራል የጸጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ዘገበ። ኦሮሚያ ሚድያ ኔትወርክ ከደቂቃዎች በፊት በሰራው ዘገባ እንዳለው ጀዋርን በቁጥጥር ሥር ለማዋል በተደረገው ጥረት የኦሮሚያ ክልል የጸጥታ ኃይሎች ከፌድራል የጸጥታ ኃይሎች ጋር ግጭት ውስጥ ገብተው ነበር። በሁለቱ ኃይሎች መካከል በተፈጠረው ፍጥጫ ጉዳት ስለመድረሱ የዘገበው ኦኤምኤን ተጨማሪ ማብራሪያ ግን አልሰጠም። የፌድራል የጸጥታ አስከባሪዎች ኃይል ጨምረው የኦሮሞ ፌድራሊስት ኮንግረስ አመራሮችን በቁጥጥር ሥር እንዳዋሉ የቴሌቭዥን ጣቢው ዘግቧል። ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ ጀዋር መሐመድ እና አቶ በቀለ ገርባ «ለጊዜው የታሰሩበት…

Read More

“የሃጫሉ ግድያ በመንግስት ሰዎች በሚገባ ታስቦ እና ታቅዶ የተፈፀመ ነው::”

የዛሬ ኣራት ቀን ኣካባቢ ኣንድ ከደህንነት ጋ ቅርብ የሆነ ሰው ኣንድ ትልቅ የኦሮሞ ሰው ሊገደል ፕላን ወጥቷል እና ትልልቆቹ የኦሮሞ ፓርቲ መሪዎችና ኣክቲቭስቶች ለደህንነታቸው እንዲጠነቀቁ ምከራቸው ብሎ ኣስጠንቅቆኝ ነበር ሲል በፌስቡክ ገጹ ገልጿል:: የተለመደ ነው በሚል ብዙም ክብደት ኣልሰጠሁትም ነገር ግን በቅርበት የማቃቸው ሰዎች ጥንቃቄ እንዲያደርጉ መክሬኣለሁ:: የሚገደለው ሰው ሃጫሉ ይሆናል ብየ ግን በፍፁም ኣላሰብኩም ነበር::”

Read More

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በታዋቂው ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገለፁ

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 22/2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በታዋቂው ሙዚቀኛ ሃጫሉ ሁንዴሳ ሞት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልፀዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሀዘን መግለጫቸው “ውድ ህይወት አጥተናል” ብለዋል። “የዚህ ድንቅና አንፀባራቂ ወጣት አርቲስት ሓጫሉ ሁንዴሳ ህይወት መቀጠፍ ከተሰማ ጀምሮ በከባድ ሀዘን ውስጥ ለምንገኝ ሁሉ መፅናናትን እመኛለሁም” ነው ያሉት። የዚህን ክፉ ድርጊት ሙሉ የፖሊስ ምርመራ ሪፖርት እየተጠባበቅን እንገኛለን […]

Read More

ሀጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ

ሀጫሉ ሁንዴሳ ከዚህ ዓለም በሞት ተለየ በኦሮምኛ ሙዚቃ ከፍተኛ ዝናን ያተረፈው ታዋቂው አርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ዛሬ ሰኔ 22/2012 ማንነታቸው ባልታወቁ ግለሰቦች በጥይት ተመቶ ሕይወቱ ማለፉን አዲስ ስታንዳርድ ዘግቧል።ሀጫሉ በገላን ኮንዶሚኒየም አካባቢ በደረሰበት በጥይት የመመታት አደጋ ወደ ጥሩነሽ ቢጂንግ ሆስፒታል በአፋጣኝ ቢወሰድም ሕይወቱን ማትረፍ እንዳልተቻለም ተገልጿል።

Read More