የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሁሉም እንዲረባረብ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2012(ኢዜአ) የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሁሉም እንዲረባረብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀርቧል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ሃለፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ በሚመለከት መግለጫ ሰተዋል። በመግለጫቸውም፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከአዲስ አበባ ውጪ በክልል ከተሞች መከሰቱን ተናግረው የተገኙት ሰዎች የውጪ አገር የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ከአሜሪካ እና ዱባይ […]

Read More

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ሁሉም በኃላፊነት እንዲንቀሳቀስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2012(ኢዜአ) የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሁሉም በኃላፊነት እንዲንቀሳቀስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተቋቋመው ንዑስ ኮሚቴ እስካሁን ድረስ ባከናወናቸው ሥራዎች ላይ ዝርዝር የአፈጻጸም ግምገማዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። በዝርዝር የአፈጻጸም ግምገማው ላይ በመመስረት ለወደፊቱ ምን መደረግ እንዳለበትም አቅጣዎች መቀመጣቸውን ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ […]

Read More

በማዕከላዊ ጎንደር በህገ-ወጥ መንገድ 3ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት ሲያጓጉዝ የነበረ አሽከርካሪ ተያዘ

ጎንደር መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) በማእከላዊ ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ በህገ-ወጥ መንገድ 3ሺህ ሊትር የምግብ ዘይት በጭነት መኪና ሲያጓጉዝ የነበረ አሽከርካሪ መያዙን የወረዳው ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ። የጽህፈት ቤቱ ሃላፊ ኢንስፔክተር በጋሻው ሽባባው ለኢዜአ እንደተናገሩት በቁጥጥር ስር የዋለው የምግብ ዘይት በመንግስት ድጎማ ለህብረተሰቡ ይቀርብ የነበረ መሆኑ ተረጋግጧል። መነሻውን ባህርዳር በማድረግ ትንናት ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ ወደ […]

Read More

በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች ሚኒስትሮች ስለ ኮሮናቫይረስ የጥንቃቄ መልእክት አስተላለፉ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እና የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በአዲስ አበባ በመዘዋወር ስለ ኮሮናቫይረስ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል። የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ በስድስት ኪሎ፣ አራት ኪሎና ፒያሳ አካባቢዎች በመዘዋወር የኮሮናቫይረስ ጥንቃቄ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። በመልእክታቸውም የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የመንግስትና የህክምና ባለሙያዎችን ትእዛዝ መተግበር ያስፍልጋል ብለዋል። ይህ […]

Read More

የ2012 ሀገራዊ ምርጫ በተያዘለት የጊዜ ሰሌዳ ማካሄድ እንደማይቻል ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ

መጋቢት 22፣ 2012 (ኢዜአ) የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ መከሰቱን ተከትሎ በተፈጠረው አስቸጋሪ ሁኔታ የተነሳ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት ምርጫውን ማካሄድ እንደማይችል ገለፀ። ቦርዱ እንዳስታወቀው ይህንኑ በመረዳት ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ በመሰረዝ በሰሌዳው መሰረት መከናወን ያለባቸው ተግባራት ለጊዜው እንዲቆሙ መወሰኑን አስታውቋል። የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ የምርጫ 2012 ኦፕሬሽን እቅድ እና የጊዜ ሰሌዳ […]

Read More

ሚኒስትሮች በአዲስ አበባ በመዘዋወር በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩት ወልደማርያም በመዲናዋ የተለያዩ አካባቢዎች በመዘዋወር በኮሮናቫይረስ ዙሪያ የጥንቃቄ ለኅብረተቡ መልእክት አስተላልፈዋል ፡፡ በዛሬው እለት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ሒሩትን ጨምሮ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶክተር ፍጹም አሰፋ፣ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ እንዲሁም ሌሎች በአዲስ አበባ በመዘዋወር የጥንቃቄ መልእክት አስተላልፈዋል።፣ ፕሮፌሰር ሒሩት በተለይ በጆሞና በኃይሌ ጋርመንት አካባቢ በመዘዋወር ባስተላለፉት መልዕክት ህብረተሰቡ አካላዊ ርቀትን እንዲጠብቅ  አሳስበዋል። […]

Read More

ሁዋጂያን ግሩፕ የተባለው የቻይና ኩባንያ ለትምህርት ሚኒስቴር 30 ሺህ የፊት ማስክ በስጦታ አበረከተ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) ሀዋጂያን ግሩፕ የተባለው የቻይና ኩባንያ 30 ሺህ የፊትና አፍ መሸፈኛ ጭንብሎችን ለኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር በስጦታ አበረከተ። የሁዋጂያን ግሩፕ ዳይሬክተር ዶክተር ግሬስ ዥንሁ በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል እየተደረገ ላለው ጥረት ኩባንያው የጀመረውን ድጋፍ አጠንክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ጌታሁን መኩሪያ ስጦታውን በመረከብ ለኩባንያው ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የተገኘው ድጋፍ በዘጠኙ ክልሎችና ሁለቱ የከተማ አስተዳደሮች በትምህርቱ ዘርፍ ለተሰማሩ […]

Read More

በአማራ ክልል 7ሺህ 650 የህግ ታራሚዎች በይቅርታ ተለቀቁ

ባህርዳር መጋቢት 22/2012 በአማራ ክልል ከኮሮና ቫይረስ መከላከል ጋር ተያይዞ ከ7ሺህ 600 በላይ ለሚሆኑ የህግ ታራሚዎች ይቅርታ መድረጉን የክልሉ ጠቅላይ አቃቤ ህግ አስታወቀ። ጠቅላይ አቃቤ ህጉ አቶ ገረመው ገብረፃድቅ እንደገለጹት የፌዴራል መንግስት ወረርሽኙን ለመከላከል ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት እስረኞቹ በልዩ ይቅርታ እንዲለቀቁ ተወስኗል። በዚህም በዕድሜ የገፉ፣ የሚያጠቡ እናቶች፣ ለአመክሮ እስከ አንድ ዓመት የቀራቸውና በቀላል እስራት የተቀጡ 7 ሺህ […]

Read More

በአዲስ አበባ ምርት የደበቁ እና ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ ከ2 ሺህ በላይ የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ ተወሰደ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ በኮሮናቫይረስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ ተጠቅመው ምርት ደብቀዋል፤ ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪም አድርገዋል ባላቸው 2 ሺህ 70 የንግድ ተቋማት ላይ እርምጃ መውስዱን አስታወቀ። የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ በኮሮና ቫይረስ የተፈጠረውን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ የዋጋ ጭማሪ እና ሌሎች ህግ ወጥ ተግባራትን የሚፈፅሙ የንግዱ ማህበሰብ አካላትን ማስጠንቀቁ ይታወሳል። […]

Read More

በደሴ ከተማና በሰሜን ወሎ ዞን ኮሮናን ለመከላከል የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ ።

ደሴ፣ወልዲያ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) በደሴ ከተማና በሰሜን ወሎ ዞን ባለሃብቶችና ነዋሪዎች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚደረገውን ጥረት ለማጠናከር የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ ። የደሴ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል 100 ሚሊዮን ብር የማሰባሰብ ስራ ጀምሯል ። ከደሴ ከተማ ባለሃብቶች መካከል አቶ ኡመር ብርቁ ለኢዜአ አንደገለፁት የኮሮና ቫይረስን መከላከል ለመንግስት ብቻ ተገፍቶ የሚሰጥ አጀንዳ አይደለም። አሁን […]

Read More