የተቋረጠውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ለማስቀጠል በቴክኖሎጂ የታገዘ እንቅስቃሴ ተጀምሯል

አዲስ አበባ, ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) በኮሮናቫይረስ ምክንያት የተቋረጠውን የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ለማስቀጠል በቴክኖሎጂ የታገዘ እንቅስቃሴ መጀመሩን የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ገለጸ። ሚኒስቴሩ ”የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና በዘመነ ኮቪድ” በሚል መሪ ሀሳብ ዛሬ የቪዲዮ ፓናል ውይይት አካሂዷል።    በውይይቱ ላይ የዘርፉ ምሁራንና ባለድርሻ አካላት የተሳተፉበት ሲሆን ዘርፉ በወረርሽኙ ምክንያት የተጋረጠበት ፈተናዎች፣ የመፍትሔ ሀሳቦችና የአገራት ተሞከሮዎች […]

Read More

በቤይሩት ይኖሩ የነበሩ 323 ዜጎች ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) በሊባኖስ ቤይሩት ይኖሩ የነበሩ 323 ዜጎች ዛሬ አዲስ አበባ ገቡ። የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ ጀምሮ በተለይ በመካከለኛው ምስራቅ በሚገኙ አገሮች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ለችግር ተጋልጠዋል። በሊባኖስ ቤይሩት ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ዜጎችም በወረርሽኙ መስፋፋት ምክንያት በችግር ውስጥ እንደነበሩ የሚታወቅ ነው። ዜጎቹን ወደ አገራቸው ለመመለስ የኢትዮጵያ መንግስት ሲሰራ መቆየቱን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የቆንጽላ ጉዳዮች […]

Read More

በነገሌ ከተማ በግብርና ምርቶች ላይ የተደረገው የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ነዋሪዎች ቅሬታቸውን ገለጹ

ነገሌ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) በነገሌ ከተማ የግብርና ምርቶችና ሸቀጣ ሸቀጦች ላይ የተደረገው ተገቢ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ ቅሬታ እንዳሳደረባቸው በከተማው አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ነዋሪዎች ገለጹ። የተጋነነ ዋጋ በመጨመር ሕዝብን ለማማረር የሚሰሩ ነጋዴዎች ላይ ሕጋዊ እርምጃ ለመውሰድ እየሰራ መሆኑን የከተማ ንግድ ጽሕፈት ቤት አስታውቋል። የከተማው ነዋሪ ወይዘሮ አዳነች ገሠሠ በሰሞኑ ገበያ በዋና ዋና የግብርና ምርቶች ላይ በኪሎ […]

Read More

የአዲስ አበባ በጎፈቃድ ወጣቶች ማኅበር ኮቪድ-19 የመከላከል ሥራ አጠናክሮ እንደሚሰራ ገለጸ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት22/2012 (ኢዜአ) የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተ ጀምሮ እጅ የማስታጠብ ንቅናቄ፣ ሀብት የማሰባሰብና ለተጎዱ ወገኖች ለመድረስ እየሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ በጎፈቃድ ወጣቶች ማኅበር አስታወቀ። የበጎፈቃድ ማኅበር አመራር አባል ወጣት ዮናስ ምትኩ ተቀዛቅዞ የነበረው የእጅ ማስታጠብና ቫይረሱን የመከላከል ሥራ አጠናክሮ ለመቀጠል ፕሮግራም መንደፋቸውን ገልጿል። የእጅ ማስታጠቡን ተግባር ለማስቀጠል ከዚህ በፊት ከነበሩት በተጨማሪ የውኃ ማጠራቀሚያ ታንከሮችና የንጽሕና […]

Read More

አዋጁን ተላልፈው ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ ሰዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል—የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012  (ኢዜአ) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅን በመተላለፍ ሰላማዊ ሰልፍ የሚጠሩ ሰዎች ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ኮሙኒኬሽን ቢሮ አስታወቀ።

የክልሉ&nbsp…

Read More

አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ለኮሮና መከላከል አንድ ሚሊዮን የሚገመት ድጋፍ አደረገ

አሶሳ፣ ግንቦት 22 /2012 (ኢዜአ) አሶሳ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል የሚውል አንድ ሚሊዮን ብር የሚገመት ምግብና የተለያዩ ግብአቶችን ለቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ኮሮና ቫይረስ መከላከል ግብረ ኃይል ዛሬ አስረከበ። የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና የኮሮና መከላከል ግብረኃይል ሰብሳቢ አቶ አሻድሊ ሐሰን ድጋፉን ከተረከቡ በኋላ እንደተናሩት በክልሉ ቫይረሱን ለመከላከል የሚደረግው ጥረት በሁሉም ባለድርሻ አካላት ሊታገዝ ይገባል። ይህም […]

Read More

የወረዳው አስተዳደር ከ500 ሺህ ብር በላይ ወጪ ለአቅመ ደካማ ያስገነባውን ቤት አስረከበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) በጉለሌ ክፍለ ከተማ የወረዳ ስምንት አስተዳደር ከ500 ሺህ ብር በላይ ወጪ በማድረግ ያስገነባውን ቤት በወረዳው ነዋሪ ለሆኑ አቅመ ደካማ አባውራ አስረከበ። የወረዳው ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰለሞን ታደሰ በቤት ርክክቡ ወቅት እንዳሉት የቤት ግንባታና እድሳት ሥራ እየተከናወነ ያለውን ለረጅም ዓመታት በቤት እጦት ችግር ውስጥ ያሉ የወረዳው ነዋሪዎችን ለመደገፍ በማሰብ ነው። […]

Read More

ለሕዳሴ ግድብ ድጋፋቸውን እንደሚያጠናክሩ በባሕርዳር የመንግሥት ሠራተኞች ገለጹ

ባሕርዳር፣ ግንቦት 22/2012  ( ኢዜአ) ለታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ግንባታ ሲያደርጉ የነበረውን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ በባሕርዳር ከተማ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ የመንግሥት ሠራተኞች ገለጹ። ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለተከታታይ ዓመታት በወር ደመወዛቸው ቦንድ በመግዛት ሲደግፉ መቆየታቸውን ሠራተኞቹ አውስተዋል። ከሠራተኞቹ መካከል አቶ ገነቱ ጥሩነህ እንዳሉት ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷ የሆነው የዓባይ ወንዝ ለዘመናት ወደ ባዕድ አገር በመፍሰስ ሲባክን […]

Read More

በሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ሁሉም ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) የፊታችን ዓርብ በሚጀመረው የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብር እያንዳንዱ ዜጋ የበኩሉን ሚና እንዲወጣ የሀገር አቀፍ አርንጓዴ አሻራ ኮሚቴ አባላት ጥሪ አቀረቡ። የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብሩ የኮሮናቫይረስ ሥርጭትን ባገናዘበ መልኩ እንዲከናወን የሚያስችል ሥልት መቀየሱም ተገልጿል። ኢትዮጵያ በዘንድሮው ክረምት አምስት ቢሊዮን ችግኞችን ለመትከል የሚያስችል ዕቅድ ነድፋ የዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነች ትገኛለች። የችግኝ ተከላ ሥራውም […]

Read More