የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ኮሮናን ለመከላከል ውሳኔዎችን አሳለፈ

ጋምቤላ፤ መጋቢት 23/2012 (ኢዜአ) የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለ14 ቀናት ተፈፃሚ የሚሆኑ የተለያዩ ውሳኔዎች  ማሳለፉን አስታወቀ።    የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ውሳኔዎቹ የተላለፉት የክልሉ መንግስት ካቢኔ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ  ሲሆን ተግባራዊ የሚሆኑትም  ከመጋቢት 23/ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በውሳኔው መሰረትም ከመሃል ሀገርና ከአጎራባች ክልሎች ወደ ክልሉ የሚገቡና የሚወጡ የህዝብ […]

Read More

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ስለኮሮናቫይረስ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ አከናወኑ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2012( ኢዜአ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚስተዋልበት መርካቶ አካባቢ በመዘዋወር ነው ስለኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ያከናወኑት።  አቶ መላኩ አለበል በቅስቀሳው ወቅት ነጋዴውና ሸማቹ ማህበረሰብ ራሱን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን የጥንቃቄ መልዕክት መተግበር እንዳለበት ገልፀዋል። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በግብይት ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎችም መልዕክት አስተላልፈዋል። […]

Read More

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል … ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2012( ኢዜአ) ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ለኮሮናቫይረስ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት በማስገባት ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስታወቀዋል። የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል ከመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም […]

Read More

የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ታይቶበት ህይወቱ ያለፈ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንደነበረበት እየተጣራ ነው

አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 23/2012( ኢዜአ) ከሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክም ሲደረግለት የነበረ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ ዛሬ ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ግለሰቡ በኮሮናቫይረስ ስለመያዙ ለማጣራት ናሙና ተወስዶ ምርመራ እየተደረገበት ነው። የጤና ሚኒስትረ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ አካሄዷል። […]

Read More

በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ተጨማሪ ሰው መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2012( ኢዜአ)የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ባካሄደው ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በማረጋገጡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ስድስት (26) መድረሱን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም […]

Read More

ህዝበ ሙስሊሙ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የተላለፉ ውሳኔዎችን ገቢራዊ እንዲያደርግ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2012(ኢዜአ) በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የኡለማዎች ምክር ቤት የኮሮናቨይረስን ለመከላከል የተላለፈውን ውሳኔ ህዝበ ሙስሊሙ ገቢራዊ ሊያደርገው እንደሚገባ ጥሪ ቀረበ። ምክር ቤቱ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን መከላከል የሚያስችሉ ውሳኔዎችን ዛሬ አሳልፏል። በውሳኔው መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የቫይረሱ ስርጭት መቆሙ በሚለከታቸው የመንግስት አካላት እስኪረጋገጥ ድረስ  በህብረት መስገድ (የጁመአ እና ጀመዓ) ሰላት ከልክሏል። በገጠርም ሆነ በከተማ በስብሰባ […]

Read More

በምዕራብ ኦሮሚያ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ዳግም እንዲጀመር ተወሰነ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) በምዕራብ ኦሮሚያ የተወሰኑ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ ዳግም እንዲጀምር መወሰኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት አስታወቀ። መንግስት ከዚህ በኋላ ማንኛውንም ስርዓት አልበኝነት እንደማይታገስና የሕግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እንደሚሰራ የክልሉ ፕሬዚዳንት ተናግረዋል። የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በተለይም በምዕራብና ደቡብ ምስራቅ ኦሮሚያ ያለውን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክተው መግለጫ […]

Read More

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች ለኮሮናቫይረስ መከላከያ የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለገሱ

አዲስ አበባ፣መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ሥራ እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለገሱ። እንደ አውሮፓውያን የዘመን ቀመር በታህሳስ ወር 2019 በቻይና ሁቤይ ግዛት ውሃን ከተማ የተከሰተው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን አዳርሷል። በዚህም እስካሁን ከ800 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፤ ከ33 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ህይወታቸው አልፏል። በኢትዮጵያ ቫይረሱ ከተከሰተበት መጋቢት 3 […]

Read More

ለኮሮናቫይርስ መከላከያ በዛሬው እለት ብቻ ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2012( ኢዜአ) በኢትዮጵያ ኮቪድ- 19ን ለመከላከል እየተደረገ ባለው የገንዘብ ማሰባሰብ በዛሬው ዕለት ብቻ ከ57 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ ተገኘ።  ድጋፉን ያደረጉት 12 የተለያዩ ድርጅቶች፣ ኩባንያዎችና ባንክች በሰላም ሚኒስቴር ተገኝተው ለኮቪድ-19 ብሔራዊ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል። ድጋፍ ካደረጉት መካከል ሜድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ 20 ሚሊዮን ብር ሲሰጥ ፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል። […]

Read More

የሐረሪ፣ አፋር ና ሶማሌ ክልሎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የተለያየ እገዳዎች መጣላቸውን ገለፁ

መጋቢት 22/2012 (ኢዜአ )የሀረሪ ፣ አፋርና ሶማሌ ክልሎች ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ የተለያየ እገዳዎች ማስተላለፋቸውን ገለፁ ።  የሀረሪ ክልል የመንግስት  ኮሙዩኒኬሽን  ጉዳዮች  ጽህፈት  ቤት  እንደገለፀው የክልሉ መንግስት በተለያዩ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ላይ እገዳዎች አስተላልፏል ። ጽህፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ የክልሉ ካቢኔ መጋቢት 21/2012 ዓ.ም ባካሔደው አስቸኳይ ስብሰባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከልና ለመቆጣጠር እንዲቻል በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ላይ እገዳ የሚጥል ባለ ሰባት ነጥብ መግለጫ አውጥቷል […]

Read More