የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ኮሮናን ለመከላከል ውሳኔዎችን አሳለፈ

ጋምቤላ፤ መጋቢት 23/2012 (ኢዜአ) የጋምቤላ ክልላዊ መንግስት ኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለ14 ቀናት ተፈፃሚ የሚሆኑ የተለያዩ ውሳኔዎች  ማሳለፉን አስታወቀ።    የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት ውሳኔዎቹ የተላለፉት የክልሉ መንግስት ካቢኔ ትናንት ባካሄደው ስብሰባ  ሲሆን ተግባራዊ የሚሆኑትም  ከመጋቢት 23/ 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በውሳኔው መሰረትም ከመሃል ሀገርና ከአጎራባች ክልሎች ወደ ክልሉ የሚገቡና የሚወጡ የህዝብ […]

Read More

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ስለኮሮናቫይረስ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ አከናወኑ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2012( ኢዜአ) የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከፍተኛ የንግድ እንቅስቃሴ በሚስተዋልበት መርካቶ አካባቢ በመዘዋወር ነው ስለኮሮናቫይረስ መከላከያ መንገዶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ያከናወኑት።  አቶ መላኩ አለበል በቅስቀሳው ወቅት ነጋዴውና ሸማቹ ማህበረሰብ ራሱን ከኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የጤና ባለሙያዎች የሚያስተላልፉትን የጥንቃቄ መልዕክት መተግበር እንዳለበት ገልፀዋል። የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በግብይት ወቅት መደረግ ስላለባቸው ጥንቃቄዎችም መልዕክት አስተላልፈዋል። […]

Read More

ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ ይቀጥላል … ዶክተር ሊያ ታደሰ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2012( ኢዜአ) ህጋዊ ባልሆነ መንገድ ከግዴታ ለይቶ ማቆያ በሚወጡ ሰዎች ላይ የሚወሰደው ህጋዊ እርምጃ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ለኮሮናቫይረስ የሚያስፈልጉ ግብአቶችን ከአገር ውስጥና ከውጭ ተቋማት በማስገባት ያለውን አገልግሎት ለማሻሻል ጥረት እየተደረገ መሆኑንም ሚኒስትሯ አስታወቀዋል። የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ስርጭትን ለመከላከል ከመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከሌሊቱ ስድስት ሰዓት ጀምሮ ማንኛውም […]

Read More

የሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ታይቶበት ህይወቱ ያለፈ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ የኮሮናቫይረስ እንደነበረበት እየተጣራ ነው

አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 23/2012( ኢዜአ) ከሳምባ ምች ህመም ምልክቶች ጋር በተያያዘ ህክም ሲደረግለት የነበረ የ68 ዓመት ኢትዮጵያዊ ዛሬ ህይወቱ ማለፉን የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ገለጹ። ግለሰቡ በኮሮናቫይረስ ስለመያዙ ለማጣራት ናሙና ተወስዶ ምርመራ እየተደረገበት ነው። የጤና ሚኒስትረ ዶክተር ሊያ ታደሰ ለኢዜአ እንደተናገሩት፤ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ አካሄዷል። […]

Read More

በአምስት የስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች የኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራ እየተከናወነ ነው

አሶሳ ኢዜአ መጋቢት 23 ቀን 2012 ዓም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል በአምስት የስደተኞች መጠለያ ጣብያዎች የሚገኙ ከ60 ሺህ በላይ ስደተኞች ከኮሮና ቫይረስ የመከላከል ስራ እየተከናወነ መሆኑን ተገለጠ።በስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አስተዳደር ጉዳይ የአሶሳ ማስተባበርያ ሃላፊ አቶ አምደወርቅ የኋላወርቅ ለኢዜአ እንዳሉት በክልሉ ሸርቆሌ ፣ ቶንጎ ፣ ባምባ ፣ ፆሬና ጉሬ የሚባሉ የስደተኞች መጠለያ ጣቢያዎች ይገኛሉ። በጣቢያዎቹ ቁሳቁሶችን ማቅረብ […]

Read More

በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29 ደረሰ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 23/2012  (ኢዜአ) በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 29  መረድረሱን የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡ የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት  እንዳስታወቀው ይህ መረጃ እስከ ተጠናቀረበት ሰአት ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 68 የላብራቶሪ ምርመራ  በማድረግ  በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ተጨማሪ ሶስት (3) ሰዎች መገኘታቸውን አረጋግጧል። ይህም  በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርን ሃያ ዘጠኝ (29)  ማድረሱን […]

Read More

ኮሮናቫይረስን እንከላከላለን ፤ ግድቡን እንጨርሳለን – ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ

 አዲስ አበባ መጋቢት 23/2012  (ኢዜአ) ”ኮሮናቫይረስን እንከላከላለን ፤ ግድቡን እንጨርሳለን” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ መልዕክት አስተላለፉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢዜአ በላኩት መግለጫ እንዳስታወቁት፤ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ጉልህ ፈተናዎች ገጥመዋታል። አንደኛው የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ራሱ የሕዳሴ ግድብ ግንባታ መሆኑን ገልጸዋል። የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ የሰው ልጅ ትልቅ ጸጋ የሆነውን ህይወት ለመንጠቅ ”የእያንዳንዳችን በር እያንኳኳ ከደጃችን ቆሟል” ብለዋል። ”የሕዳሴ ግድባችን […]

Read More

በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ተጨማሪ ሰው መገኘቱን ጤና ሚኒስቴር ገለጸ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 22/2012( ኢዜአ)የኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ ባካሄደው ተጨማሪ የላብራቶሪ ምርመራ አንድ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሰው በማረጋገጡ በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ሃያ ስድስት (26) መድረሱን ጤና ሚኒስቴር ገልጿል፡፡ በቫይረሱ መያዙ የተረጋገጠው ግለሰብ የ42 ዓመት የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የአስገዳጅ ለይቶ ማቆያ ከመጀመሩ አስቀድሞ መጋቢት 9/2012 ከአውስትራሊያ አዲስ አበባ እንዲሁም […]

Read More

የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሁሉም እንዲረባረብ ጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2012(ኢዜአ) የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ሁሉም እንዲረባረብ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ጥሪ አቀርቧል። የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ፕሬስ ሴክሬተሪያት ሃለፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል እየተሰራ ያለውን ስራ በሚመለከት መግለጫ ሰተዋል። በመግለጫቸውም፤ የኮሮናቫይረስ ስርጭት ከአዲስ አበባ ውጪ በክልል ከተሞች መከሰቱን ተናግረው የተገኙት ሰዎች የውጪ አገር የጉዞ ታሪክ የነበራቸው ከአሜሪካ እና ዱባይ […]

Read More

የኮሮናቫይረስን ለመከላከል ሁሉም በኃላፊነት እንዲንቀሳቀስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ

አዲስ አበባ መጋቢት 22/2012(ኢዜአ) የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ሁሉም በኃላፊነት እንዲንቀሳቀስ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን አሳሰቡ።  ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኮሮናቫይረስን ለመከላከል በሚኒስትሮች ምክር ቤት የተቋቋመው ንዑስ ኮሚቴ እስካሁን ድረስ ባከናወናቸው ሥራዎች ላይ ዝርዝር የአፈጻጸም ግምገማዎችን አስመልክተው መግለጫ ሰጥተዋል። በዝርዝር የአፈጻጸም ግምገማው ላይ በመመስረት ለወደፊቱ ምን መደረግ እንዳለበትም አቅጣዎች መቀመጣቸውን ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመግለጫቸው በኢትዮጵያ […]

Read More