በዋሽንግተን ዲሲ ሊካሄድ የነበረው ታላቁ ሩጫ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለሌላ ጊዜ ተላለፈ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 15፣ 2012 (ኢዜአ) በአሜሪካ በዋሽንግተን ዲሲ በየዓመቱ ይካሄድ የነበረው ታላቅ ሩጫ ውድድር በኮሮና ቫይረስ ወረሽኝ ምክንያት ለጥቅምት ተላለፈ። በ2010 ዓ.ም ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ በሰሜን አሜሪካ በሦስት ከተሞች ተገኝተው፣ ከተፈጠረው ለውጥ ጋር ተያይዞ ከኢትዮጵያውያን ጋር መወያየታቸው ይታወሳል። በዋሽንግተን በነበረው የጠቅላይ ሚኒስትሩና የኢትዮጵያውያን ፕሮግራም  የከተማዋ ከንቲባ መሪያል ባውሰር ቀኑን ‹‹የኢትዮጵያውያን ቀን በዲሲ›› ተብሎ እንዲከበር መወሰናቸውም አይዘነጋም። […]

Read More

አትሌቶች ለኮሮና ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ሆቴል ገብተው በጋራ ልምምድ ቢሰሩ የተሻለ ነው– አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ

ኦሎምፒክ ቡድኑ የተመረጡ አትሌቶች የኮሮና ቫይረሱ ተጋላጭነታቸውን ለመቀነስ ሆቴል ገብተው ልምምዳቸውን በጋራ ቢሰሩ የተሻለ መሆኑን አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ ገለጸ። የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በመጪው ክረምት በቶኪዮ የሚካሄደውን የኦሎምፒክ ጨዋታዎች ውድድር እንደማይሰርዝ አስታውቋል። የኢትዮጵያ አሊምፒክ ኮሚቴም የቶኪዮ ኦሎምፒክ የአትሌቶችን ቅድመ ዝግጅት በተመለከተ መግለጫ ሰጥቷል። በመግለጫው ላይ የተገኘው ሻለቃ አትሌት ሃይሌ ገብረስላሴ የቶኪዮ ኦሎምፒክ እንደሌሎች ውድድሮች ይራዘማል የሚል […]

Read More

በቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ሙገር ሲሚንቶን አሸነፈ

አዲስ አበባ መጋቢት 07/2012 (ኢዜአ) በሐበሻ ሲሚንቶ የወንዶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ወላይታ ድቻ ሙገር ሲሚንቶን አሸንፏል። መደወላቡ ዩኒቨርሲቲ መሪነቱን አጠናክሯል። የፕሪሚየር ሊጉ 10ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ትናንትና እና ከትናንት በስቲያ በክልል ከተሞችና በአዲስ አበባ ተካሂዷል። በሳምንቱ በፕሪሚየር ሊጉ ይጠበቅ የነበረው የአምናው የሊጉ አሸናፊ ወላይታ ድቻ እና ሙገር ሲሚንቶ ጨዋታ ባለሜዳው ወላይታ ድቻ በአራት የጨዋታ ክፍለ ጊዜ 3 ለ 1 አሸንፏል። […]

Read More

በትግራይ ክልል አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ተጀመረ

መቀሌ፤ መጋቢት 5/2012 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል አቀፍ የአትሌቲክስ ውድርር ዛሬ በመቐለ ተጀምሯል።  የትግራይ ክልል አትሌቲክስ ፌደሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ማሞ እንደገለፁት ውድድሩ የፊታችን ሚያዝያ ወር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚካሄደው የአትሌቲክስ ሻምፕዮና ክልሉን ወክለው የሚሳተፉ  ብቃት ያላቸው አትሌቶችን ለመምረጥ የተዘጋጀ ነው ። ዛሬ የተጀመረው ውድድር በተለያዩ የአትሌቲክስ ዘርፎች ለአንድ ሳምንት እንደሚካሔድም አቶ ጌታቸው ተናግረዋል ። በክልሉ የአትሌቲክስ ውድድር ዳኞች ፕሬዚዳንት  አቶ ቢንያም ሂወት በበኩላቸው ውድድሩ […]

Read More

ኢትዮጵያ የምታስተናግደው የምስራቅ አፍሪካ የእጅ ኳስ ውድድር በሚያዚያ ወር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 3/2012(ኢዜአ) ላልተወሰነ ጊዜ ተራዝሞ የነበረው የምስራቅ አፍሪካ የዞን አምስት የታዳጊዎች እጅ ኳስ ውድድር በሚያዚያ 2012 ዓ.ም እንደሚካሄድ ተገለጸ። ዓለም አቀፉ የእጅ ኳስ ፌዴሬሽን ውድድሩን ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለማካሄድ ወስኖ ነበር። ፌዴሬሽኑ ከሁለት ሳምንት በፊት ውድድሩ ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን ቢገልጽም ምክንያቱን ግን አላሳወቀም ነበር። በዚሁ መሰረት […]

Read More

ብሔራዊ ቡድኑ ለአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታ የሚያደርገውን ዝግጅት መጋቢት 6 ይጀምራል

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 1/2012(ኢዜአ) የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከኒጀር አቻው ጋር ለሚያደርገው የአፍሪካ ዋንጫ የደርሶ መልስ የማጣሪያ ጨዋታ ከመጋቢት 6 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ልምምድ እንደሚያደርግ ተገለጸ። የብሔራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራህቱ ቡድኑ ለሚያደርጋቸው ልምምዶች የተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል። በጥር ወር 2013 ዓ.ም በካሜሮን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው 33ኛው የአፍሪካ ዋንጫ አገሮች በውድድሩ ላይ ለመሳተፍ ከህዳር ወር 2012 […]

Read More

በቼዝ ውድድር ያሸነፉ ስፖርተኞች መቀሌ ሲገቡ አቀባበል ተደረገላቸው

መቀሌ፣ የካቲት 01/2012(ኢዜአ) በሀገር አቀፍ የቼዝ ውደደር ተሳትፈው ሁለት ዋንጫዎችን ያገኙት ተወዳዳሪዎች አገራቸውን ወክለው የመወዳደር እድል በማግኘታቸው ትናንት መቀሌ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው። የትግራይ ቼዝ ፌደሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት አቶ መልአኩ ቴድሮስ እንደገለፁት ኢትዮጵያን ወክለው እንዲወዳደሩ የተመረጡ ሁለቱ ተወዳዳሪዎች በአዲስ አበባ ከተማ ከየካቲት 16 እስከ የካቲት 28 ቀን 2012 ዓም በተካሄደው አገር አቀፍ የቼዝ ውድድር በአሸናፊነት ያጠናቀቁ […]

Read More

የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 30/2012 ( ኢዜአ) የሐበሻ ሲሚንቶ የሴቶች ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ የመጀመሪያ ዙር ውድድር ትናንት በተካሄዱ ጨዋታዎች ፍጻሜውን አግኝቷል።  ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ፣ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ ጌታዘሩ ስፖርት ክለብና ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የፕሪሚየር ሊጉ ተሳታፊ ክለቦች ናቸው። ትናንት በአዲስ አበባ ትንሿ ሁለገብ ስታዲየም ሁለት ጨዋታዎች ተደርገዋል። የፕሪሚየር ሊጉ መሪ ብሔራዊ አልኮልና አረቄ ፋብሪካ ጌታዘሩ ስፖርት ክለብን በአምስት የጨዋታ ክፍለ […]

Read More

ድሬዳዋ ከነማ ሃዋሳ ከተማን 3 ለ 1 አሸነፈ

የካቲት 29/2012 (ኢዜአ) ራሱን በአዳዲስ ተጨዋቾች ያዋቀረው ድሬዳዋ ከነማ በሜዳው ሃዋሣ ከተማን 3ለ1 ረቷል። ደረጃውን ያሻሻለበትን ውጤት ያስመዘገበው ድሬዳዋ ከነማ ከሜዳው ውጪ ማሸነፉን ተናግረዋል፡፡ በ16ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ተጋጣሚውን ያሸነፈው ድሬዳዋ ከተማ ከተጋጣሚው ቡድን ተመጣጣኝ ፉክክር ያጋጠመው ቢሆንም ኢላማቸውን የጠበቁ ሙከራዎችን በማድረግ ውጤታማ መሆን ችሏል። ይህንን ተከትሎ በ14ኛው ደቂቃ ሪቻርድ ኦዶንጎ የመጀመሪያውን ግብ […]

Read More

የሊጉ የሁለተኛ ዙር ውድድር ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ይካሄዳሉ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 27/2012 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የሁለተኛ ዙር ውድድር ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላሉ። የሊጉ የመጀመሪያ ዙር የውድድር መርሃ ግብር ከሁለት ሳምንታት ዕረፍት ጊዜ በኋላ ነገና ከነገ በስቲያ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይጀመራሉ። በዚህም ሁለት ጨዋታዎች ነገ ፣ቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታዎች ደግሞ እሁድ በክልልና በአዲስ አበባ ስታዲዬሞች ይደረጋሉ። ነገ ከቀኑ በ9 ሰዓት ፋሲል ከነማ ከአዳማ […]

Read More