በግብርናው ዘርፍ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ የተጀመረው ጥረት ተስፋ ሰጭ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2012 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል በግብርናው ዘርፍ ወጣቶችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተደረገ ያለው ጥረት ተስፋ ሰጭና የሚበረታታ መሆኑን አትሌቶችና አርቲስቶች ተናገሩ። በርካታ አትሌቶችና አርቲስቶች በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ሸዋ ዞን በወጣቶች እየተከናወኑ ያሉ የአትክልትና ፍራፍሬ ልማቶችን ጎብኝተዋል። ከጎብኝዎቹ መካከል ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ አትሌቶችና  አርቲስቶች  የወጣቶችን  ተጠቃሚነት እውን ለማድርግ የክልሉ  መንግሥት  የጀመረውን  ሥራ አድንቀዋል። ወጣቶች በተለይ በገጠሩ አካባቢ ያለውን ዕውቀትና ጉልበት ተጠቅመው በልማት ሥራ ላይ በስፋት መሳተፋቸውም ጥሩ ጅምር መሆኑን ገልጸዋል። ወጣቶቹ ራሳቸውንና ቤተሰባቸውን በማገዝ ከድህነት ለመውጣት የሚያደርጉትን ጥረት ማጠናከር ይኖርባቸዋልም […]

Read More

የሰሜን ሸዋ አርሶ አደሮች በምርት ዘመኑ ግብአት እጅ በእጅ በመግዛት እየተጠቀሙ ነው

ፍቼ፣ ግንቦት 22/2ዐ12 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን አርሶ አደሮች በተያዘው የምርት ዘመን ግብአት ከብድር ይልቅ እጅ በእጅ በመግዛት እየተጠቀሙ መሆኑን የዞኑ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ጽህፈት ቤት አስታወቀ ፡፡ የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ መሳይ ወርቁ እንደገለጹት  በዞኑ 13 ወረዳዎች ቀደም ሲል ለአርሶ አደሮች  የምርት ማሳደጊያ ግብዓት የሚቀርበው በብድር ነበር። በአሁኑ ወቅት አርሶ አደሩ የቀረበለት […]

Read More

በአርሲ ዞን የልማት ስራዎች ጉብኝት ተካሄደ

አዳማ ግንቦት 21/2012( ኢዜአ ) በአርሲ ዞን ሌሙና ቢልቢሉ ወረዳ በመስኖ እየለማ ያለው አትክልትና ፍሬፍሬ ዛሬ በክልሉ መንግስት እና የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ተጎበኘ። በጎብኝቱ ወቅት በዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማዕከል የህዝብና የውጭ ግንኙነት ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አወሉ አብዲ እንደገለፁት አርሶ አደሩ መሬቱን   በኩታ ገጠም በማሰባሰብ እያካሄደ ያለው የድንችና ሌሎችንም  ሰብሎች ልማት ትልቅ ተሞክሮና ልምድ የሚወሰድበት ነው። […]

Read More

በጌዴኦ ዞን በ26 ሚሊዮን ብር የተገነቡ የውሃና የመስኖ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቁ

ዲላ፣ ግንቦት 21/2012 (ኢዜአ)  በጌዴኦ ዞን ላለፉት ሁለት ዓመታት በግንባታ ላይ የነበሩ የልማት ፕሮጀክቶች ተጠናቀው ለአገልግሎት መብቃታቸውን የዞኑ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ልማት መምሪያ ገለጸ።በዞኑ የተሰሩ የልማት ፕሮጀክቶች  በክልልና በዞን ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ተጎብኝተዋል። የመምሪያው ተወካይ አቶ ዮሐንስ ታደሰ በሰጡት ማብራሪያ በወናጎና ገደብ ወረዳዎች በመንግስት በጀት የተገነቡ የመስኖና የመጠጥ ውኃ ፕሮጀክቶች ለአገልግሎት በቅተዋል ። “የመስኖ እርሻ ለዘላቂ […]

Read More

በአማራ ክልል 3 ሺህ ሄክታር አሲዳማ መሬት በኖራ የማከም ስራ እየተካሔደ ነው

ባህርዳር/መተማ / ግንቦት 21/2012  በአማራ ክልል 3 ሺህ ሄክታር አሲዳማ መሬት በኖራ በማከም ምርታማነቱን እንዲጨምር የማድረግ ስራ እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ግብርና ቢሮ አስታወቀ።  የቢሮው የአፈር ለምነት ባለሙያ አቶ አጠቃ አይቸው ለኢዜአ እንደገለጹት በአሲዳማነት የተጎዳ የእርሻ መሬትን አክሞ ምርታማነቱን ለማሳደግ 60 ሺህ ኩንታል ኖራ በማቅረብ ጥቅም ላይ እንዲውል ይደረጋል ። እስከ አሁን 17 ሺህ 528 ኩንታል ኖራ ለአርሶ አደሮች በማሰራጨት በ5 ሺህ 170 ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ ተበትኖ ለዘር ዝግጁ ሆኗል ። ቀሪውን የኖራ ምርት ከደጀንና ከኦሮሚያ ክልል ጫንጮ የማጓጓዝ ስራ እየተከናወነ ሲሆን እስከ ሰኔ ወር አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ለአርሶ አደሮች ይሰራጫል። የኖራ ምርት ብክነትን ለመቀነስም ሳይንሳዊ አሰራሩን ተከትሎ በመስመር ከዘር ጋር ጥቅም ላይ እንደሚውል ለማድረግም እየተሰራ ይገኛል። የእርሻ መሬቱን አክሞ ምርታማነቱን ለማሻሻል እየተሰራ ያለው ተግባርም በኮሮና ምክንያት የምርት መቀነስ እንዳይከሰት የሚደረገው ጥረት አካል ነው ብለዋል። በአንድ ሄክታር የእርሻ መሬት ላይ እስከ 20 ኩንታል የኖራ ምርት እንደሚያስፈልግ ጠቅሰው በኖራ የታከመ አሲዳማ መሬት ምርታማነትን በእጥፍ ለማሳደግ ያስችላል።  ከ2010 ዓ.ም ጀምሮ አሲዳማ መሬታቸውን በማከም የሰብል ምርታማነቱን ማሳደግ እንደቻሉ የተናገሩት ደግሞ በደቡብ ጎንደር ዞን ፋርጣ ወረዳ የማይነት ቀበሌ አርሶ አደር ሰንደቄ አወቀ ናቸው። ባለፈው ዓመት በሩብ ሄክታር መሬት 10 ኩንታል ኖራን ከኮምፖስት ጋር ቀላቅለው በመጠቀም  አልምተው 80 ኩንታል ድንች ማግኘታቸውን ተናግረዋል። […]

Read More

በምሥራቅ ወለጋ ከ97 ሚሊዮን የሚበልጥ የቡና ችግኝ ለተከላ ተዘጋጀ

ነቀምቴ ፣ ግንቦት 21/2012 ( ኢዜአ) በምሥራቅ ወለጋ ዞን በመጪው ክረምት የሚተከል ከ97 ሚሊዮን የሚበልጥ የቡና ችግኝ ተዘጋጅቶ እንክብካቤ እየተደረገለት መሆኑን የዞኑ የእርሻና የተፈጥሮ ሀብት ልማት ጽህፈት ቤት ገለጸ። ችግኙ የተዘጋጀው በዞኑ 17 ወረዳዎች በሚገኙ  የመንግሥትና ግል የቡና ችግኝ ጣቢያዎች መሆኑን በጽህፈት ቤቱ የቡና ልማት ባለሙያ አቶ ነገሮ አበሹ ተናግረዋል። “የቡና ችግኝ በሽታን ለመቋቋም የሚችልና ብዙ ምርት […]

Read More

በምዕራብ ጎንደር ዞን ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ቀድሞ በሚዘሩ ሰብሎች ተሸፍኗል

መተማ፣ ግንቦት 21/2012 ( ኢዜአ) በምዕራብ ጎንደር ዞን ከኮሮና ቫይረስ መከላከል ጎን ለጎን ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት ቀድሞ በሚዘሩ ሰብሎች መሸፈኑን የዞኑ ግብርናና ገጠር ልማት መምሪያ አስታወቀ፡፡ በመምሪያው የሰብል ልማት ባለሙያ አቶ ሞገስ ጋሹ ለኢዜአ እንደገለጹት በዞኑ በዘንድሮው የመኽር አዝመራ 412 ሺህ ሄክታር መሬት በዘር ለመሸፈን ታቅዶ ወደ ስራ ተገብቷል። ከታቀደው ማሳ ውስጥ 130 ሺህ ሄክታር የሚጠጋ መሬት በባለሃብት የሚለማ ሲሆን ቀሪው ደግሞ በአርሶ አደሮች ይዞታነት የሚለማ መሆኑን አስረድተዋል፡፡ አሁን በአርሶ አደሩ ይዞታ የሚገኝ ከ30 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በማሽላና ዳጉሳ ሰብሎች የተሸፈነ ሲሆን 230 ሺህ ሄክታር መሬት በማፅዳት ለዘር ዝግጁ ሆኗል ። የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በዞኑ መስፋፋቱን ተከትሎ የጉልበት ሰራተኛ እጥረት እንዳይገጥምና ሰራተኞችም በቫይረሱ እንዳይያዙ ከወዲሁ ቅድመ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑንም አስገንዝበዋል፡፡ “በዞኑ በዋናነት ከሚመረቱ ሰሊጥ፣ ማሽላና ጥጥ በተጨማሪ እንደ አኩሪ አተር፣ ጤፍ፣ ምስር፣ ማሾ፣ ቦለቄና […]

Read More

ለአርሶ አደሩ ምርታማነት መጨመር በትኩረት እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

ደብረ ብርሃን፤ ግንቦት 20/2012 የኮሮና ስርጭትን በመከላከል የግብርና ምርታማነትን ለማሻሻልና የአርሶ አደሩን ተጠቀሚነት ለማሳደግ የብልፅግና ፓርቲ በትኩረት እንደሚሰራ የፓርቲው ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም ገለፁ። የብልጽግና ፓርቲ አመራሮች በሰሜን ሸዋ ዞን ሁለት ወረዳዎችና በደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር የመስክ ጉብኝት አካሄደዋል። ሃላፊው በጉብኝቱ ወቅት እንዳሉት የኮሮና ቫይረስ ዓለም አቀፍ ይዘት ያለውና የመከላከል ሁኔታውም አስቸጋሪ ቢሆንም […]

Read More

የመሥሪያ ቦታ ችግር እንዲፈታላቸው በሀዋሳ በወተት ላምች እርባታ የተሰማሩ ማኅበራት ጠየቁ

ሐዋሳ ፣ ግንቦት 20/2012 (ኢዜአ) ያጋጠማቸውን የመሥሪያ ቦታ ችግር እንዲፈታላቸው በሀዋሳ ከተማ በወተት ላሞች እርባታ የተሰማሩ ማኅበራት ጠየቁ። በሐዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ የተመራ የሥራ ኃላፊዎች ቡድን በከተማዋ እየተከናወኑ የሚገኙ  የግብርና ልማት ሥራዎችን ተመልክተዋል። በዚህ ወቅት የሙሉ እና ቤተሰቦቿ የወተት ከብት እርባታ ማኅበር ሰብሳቢ ወይዘሮ መሉ ጎሽሜ እንዳሉት ማኅበሩ በ2008 ዓ.ም 60 ሺህ ብር በሆነ ካፒታል […]

Read More

ኮቪድ-19 በግብርናው ዘርፍ የሚያሳድረውን ተጽዕኖ ለመቋቋም እየተሰራ ነው–የኦሮሚያ መንግሥት

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20/2012 (ኢዜአ) የኮቪድ 19 ወረርሽኝ የግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ በኢኮኖሚው ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመቋቋም እየተሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ገለጸ። የክልሉ የግብርና ዘርፍ እንቅስቃሴ ሰሞኑን ተጎብኝቷል። በምክትል ፕሬዚዳንት ማዕረግ የክልሉ መንግሥት ማህበራዊ ክላስተር አስተባባሪ አቶ አዲሱ አረጋ በዚህ ወቅት  ለኢዜአ በሰጡት አስተያየት እንደገለጹት  ” የክልሉ  መንግሥት  በግብርናው ዘርፍ ምርትና ምርታማነትን  በማሳደግ የአርሶ አደሩን  ህይወት  ለውጦ ኢኮኖሚውን ለመታደግ በመካናይዜሽን የተደገፈ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል”። በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ አስጊ የሆነው የኮሮና ቫይረስ በጤና ላይ ከሚያደርሰው ጉዳት ባለፈ፤ ኢኮኖሚውንም ክፉኛ ሊጎዳ እንደሚችል ተናግረዋል፡፡ የክልሉ መንግሥትም በተለይ በገጠሩ አካባቢ ወረርሽኙን እየተከላከለ በግብርናው ዘርፍ እያደረገ ያለውን እንቅስቃሴ  በማጠናከር ቫይረሱ በኢኮኖሚ […]

Read More