በአማራ ክልል የኮሮና ስርጭትን ለመግታት “አንቲ ቦዲ” ምርመራ ሊካሄድ ነው

ባህርዳር ሰኔ 22/2012 በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የሰውነት በሽታ መከላከል “አንቲ ቦዲ” አቅምን ለማወቅ የሚያስችል ምርመራ ከነገ ጀምሮ በባህርዳርና ደሴ ከተሞች እንደሚካሄድ የክልሉ ጤና ቢሮ አስታወቀ። የቢሮው ኃላፊና የኮሮና መከላከል ግብረ ኃይል ፀሐፊ ዶክተር መልካሙ አብቴ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደገለጹት የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተበት  ጀምሮ የተለያዩ የመከላከያ እርምጃዎች ተወስዷል። እስካሁን የቫይረሱ መከላከያ መንገዶችን በማስተማር፣ የለይቶ […]

Read More

በ24 ሰዓታት ምርመራ ተጨማሪ 157 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው፤ የ5 ሰዎችም ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22/2012 (ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 693 የላቦራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 157 ሰዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸውና የ5 ሰዎች ህይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። በአጠቃላይ በአገሪቱ ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 846 ደርሷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው 132 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 5 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 5 ሰዎች ድሬደዋ ከተማ አስተዳዳር ፣ […]

Read More

የመንግስት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት ይቀጥላል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 22/2012(ኢዜአ) በመዲናዋ በሚገኙ የመንግሥት አገልግሎት መስጫ ተቋማት ላይ የሚደረገው የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የአዲስ አበባ ምግብና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን አስታወቀ። ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በጤና ሚኒስቴር ቅጥር ግቢ ውስጥ የጸረ ተህዋሲያን ኬሚካል ርጭት አካሄዷል። የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ዓለማየሁ ሁንድማ ለኢዜአ እንደገለጹት፤ በግለሰብ ደረጃ ብቻ በሚደረግ የጥንቃቄ ተግባር የኮሮናቫይረስን የመከላከሉን ተግባር […]

Read More

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 119 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ተገኘባቸው

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2012 ( ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገው 3 ሺህ 895 የላቦራቶሪ ምርመራ 119 ሰዎች የኮሮናቫይረስ የተገኘባቸው ሲሆን የ4 ሰዎች ህይወት አልፏል። በአጠቃላይ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 689 ደርሷል። ቫይረሱ የተገኘባቸው 73 ወንዶችና 46 ሴቶች ሲሆኑ፣ ከአንድ ዓመት ሕፃን እስከ 80 ዓመት አዛውንት ይገኙበታል። በዜግነት 116 ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ 3ቱ […]

Read More

የኮሮና ወረርሽኝ በአዕምሮ ጤና ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት ራስን መጠበቅ ይገባል

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በአዕምሮ ጤና ላይ ከሚያስከትለው ጉዳት ራስን መጠበቅ እንደሚገባ የሥነ-አዕምሮ ባለሙያዎች አሳሰቡ። የሥነ- አዕምሮ ባለሙያዋ ወይዘሮ ትዝታ ሰዴቻ እንደሚሉት ዜጎች አውቀውም ይሁን ሳያውቁት በአኗኗር ዘይቤያቸው መቀየርና ሌሎች ተዛማች ችግሮች ለአዕምሮ ሕመም ይዳረጋሉ። በዓለም አቀፍ ደረጃ በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ሳቢያ  ለአዕምሮ ሕመም የሚዳረጉ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ጥናቶች አመላክተዋል። መረጃዎች እንደሚያመለክቱት በኢትዮጵያም የአዕምሮ ጤና እክል ያጋጠማቸው ዜጎች ቁጥር በሶስት እጥፍ አድጓል ነው የሚሉት። ኮቪድ-19 በባህሪው ቀድሞ ከነበረን ወደ አዲስ የአኗኗር ዘይቤ ስለሚወስድ ሰዎች አዲሱን ዘይቤ ለመላመድ በሚያደርጉት ጥረት ለጭንቀት ይዳረጋሉ። እኔና ቤተሰቤ በወረርሽኙ ብንጠቃስ፣ የኢኮኖሚ  ጫና ቢደርስብንስ የሚሉና በተጓዳኝ ሕመሞች ሳቢያ በወረርሽኙ ሊጠቁ ይችላሉ ተብለው ከሚጠቀሱ መካከል ሲሆኑ ለጭንቀት ይዳረጋሉ። በዚህ ሳቢያ ዕንቅልፍ ማጣት፣ የሰውነት መዛል፣ የሕመም ስሜቶች በተደጋጋሚ መሰማት፣ ሕመሞችን የማስተናገድ፣ ግራ የመጋባት፣ የመነጫነጭና የትኩረት ማጣት ችግሮች ይከሰታሉ። ሰዎች  ረጅም ጊዜያቸውን ስለ በሽታው መረጃ በማነፍነፍ ወይም ጨርሶ በመሸሽ  ላይ እያተኮሩ ከሆነም ለአዕምሮ ሕመም  ሊዳረጉ እንደሚችሉ ማወቅ አለባቸው ነው ያሉት ባለሙያዋ። ችግሮችን ለመቆጣጠር መፍትሄው በእጃችን ነው ያሉት ወይዘሮ ትዝታ በቅድሚያ ለአካላዊ ሰውነታችን የምንሰጠውን ያህል ለአዕምሯችንም ትኩረት መስጠት ይጠበቅብናል ብለዋል። ቤተሰብ ለዚህ ችግር እንዳይዳረግ በቤት ውስጥ ውይይትና ግልፅነትን ማስፈን፣ ራስን መቆጣጠርና […]

Read More

የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት /አተት/ ወረርሽኝን ለመከላከል በሁሉም ክልሎች ቅድመ ዝግጅት ተደርጓል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2012 ዓ.ም ( ኢዜአ) የክረምት መግባትን ተከትሎ በአገሪቷ ሁሉም ክልሎች የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት /አተት/ ወረርሽኝ እንዳይስፋፋ የመከላከል ቅድመ ዝግጅት ማድረጉን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ከክረምት መግባት አስቀድሞ የአጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት በሽታ በደቡብ፣ በኦሮሚያና በሶማሌ ክልሎች ተከስቶ እንደነበር ይታወቃል።  በሚኒስቴሩ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ዳይሬክተር አቶ አሽረፈዲን ኑር እንደገለጹት፣ በየክልሉ ለበሽታው ተጋላጭ የሆኑ አካባቢዎች ላይ የቅድመ […]

Read More

ኮቪድ-19 የመንግስት ተቋማት በስብሰባ የሚያጠፉትን ጊዜ በማስቀረት አዎንታዊ ሚና ተጫውቷል

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 21/2012 ( ኢዜአ) የመንግስት ተቋማት በስብሰባ የሚያጠፉትን ጊዜ በማስቀረት ረገድ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ አዎንታዊ ሚና መጫወቱን የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽነር በዛብህ ገብረየስ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ እንዳሉት በመንግስት ተቋማት ስብሰባ መብዛትና ለተገልጋዩ ፈጣን አገልግሎት ባለመስጠት ተደጋጋሚ ቅሬታ ይቀርብባቸዋል። ስብሰባዎቹ ጊዜና ገንዘብ ከመፍጀት ባለፈ በውጤት የማይታጀቡ መሆናቸውንም ጠቁመዋል። ይህ ሲቪል ሰርቪሱን ለተደጋጋሚ […]

Read More

የሕክምና ግብዓቶችና የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለማሟላት እየተሰራ ነው – ጤና ሚኒስቴር

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19/2012 ( ኢዜአ) ለጤና ተቋማት የሕክምና ግብዓቶችና የኢንፌክሽን መከላከያ ቁሳቁስ ለሟሟላት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገለጹ። የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፤ ለጤና ተቋማቱ በግዥ አልያም በዕርዳታ የሚገኙ የሕክምና መሳሪያዎችና ግብዓቶችን የማሰባሰብ ሥራው ተጠናክሯል ብለዋል። በተለይም በጽኑ ሕሙማን ክትትል ለሚገኙ የኮቪድ-19 ታካሚዎች የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ የሕክምና ግብዓቶችን […]

Read More

ዓለም አቀፍ ድርጅቶቹ የኢትዮጵያን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ የመከላከል ተግባር የሚያግዝ ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19/2012 ( ኢዜአ) ኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል እየከወነች ያለውን ተግባር ለመደገፍ ዋተር ኤይድ፣ የህጻናት አድን ድርጅትና ዩኒሴፍ አዲስ ፕሮጀክት ይፋ አደረጉ። ድርጅቶቹ ከኮቪድ-19 ጋር በተገናኘ በንጽህና አጠባበቅና በባህሪ ለውጥ ማምጣት በጥምረት የሚሰሩበትን አዲስ ፕሮጀክት ነው ይፋ ያደረጉት። ፕሮጀክቱ የኢትዮጵያ መንግስት የኮሮና ወረርሽኝ ስርጭትን ለመቆጣጠር የሚያደርገውን ጥረት ለመደገፍ፣ ለንጽህና አጠባበቅና የባህሪ ለውጥ ይሰራል። የመገናኛ […]

Read More

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 250 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የ8 ሰዎች ሕይወት አልፏል

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 19/2012 ( ኢዜአ) በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 5 ሺህ 414 የላቦራቶሪ ምርመራ 250 ሰዎች የኮሮናቫይረስ ሲገኝባቸው፤ የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉ ተገለጸ። 144 ሰዎች ደግሞ በትናንትናው ዕለት አገግመዋል። የጤና ሚኒስቴርና የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) ምላሽ አሰጣጥን አስመልክቶ ዛሬ ባወጡት መግለጫ እንዳመለከተው፤ በኢትዮጵያ ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 5 ሺህ 425 ደርሷል። […]

Read More