በኢትዮጵያ በኮቪድ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 25 ደረሰ

የኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ባለፈው 24 ሰአታት ውስጥ በ66 ሰዎች ላይ ባደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮቪድ19 የተያዙ ተጨማሪ ሶስት ሰዎች መኖራቸው መረጋገጡን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ ይህ መረጃ እስከ ተዘጋጀበት ሰዓት ድረስ በአጠቃላይ 1013 የላቦራቶሪ ምርመራ ማካሄዱን ያስታወቀ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን……

Read More

በምዕራብ ኦሮሚያ ተቋርጦ የነበረው የቴሌኮም አገልግሎት እንዲከፈት ተወሰነ

የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት ሽመልስ አብዲሳ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በምዕራብ ኦሮሚያ በተለይም በአራቱ የወለጋ ዞኖች ተቋርጦ የነበረው የሞባይል ኢንተርኔት እና የሰልክ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ እንዲከፍት ተወስኗል ብለዋል። አቶ ሽመልስ ባለፉት ቀናቶች በቄለም ወለጋ፣ ምእራብ እና ምስራቅ ወለጋ እንዲሁም ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ……

Read More

በኦሮሚያ ክልል የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት ታገደ

በኦሮሚያ ክልል የከተማ ውስጥ የህዝብ ትራንስፖርት መታገዱን የክልሉ መንግስት አስታወቀ። በዚህ መሰረት ታክሲ፣ ባጃጅ፣ ሞተር ሳይክል እና ጋሪ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንዲያቆሙ ተወስኗል፡፡ ሀገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርትም ሙሉ በሙሉ እንዲቀረጥ ነው የክልሉ መንግስት ውሳኔ ያሳለፈው። በክልሉ ያሉ የወረዳ ትራንስፖርቶች……

Read More

በኢትዮጵያ በኮቪድ19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 23 ደረሰ

    ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በኢትዮጵያ በኮቪድ19 የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 23 መድረሱን ይፋ አደረጉ። እስከ ዛሬ መጋቢት 21/2012  ጠዋት ድረስ የላብራቶሪ ምርመራ ከተደረገላቸው ከ800 የሚበልጡ ተጠርጣሪዎች መካከል  23 ሰዎች ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ዐቢይ አህምድ ገልጸዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ኹለት ሰዎች……

Read More

‹‹ሶደሬ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል መንግሥት ትዕዛዝ ተዘግቷል›› ዲንቁ ደያሳ

ከ70 ዓመታት በፊት በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ የተቋቋመው እና በኋላም ወደ ግሉ ዘርፍ እንዲዞር የተወሰነው የሶደሬ ሪዞርት በኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት ትዕዛዝ ባሳለፍነው ሐሙስ መጋቢት17/2012 መዘጋቱን ሪዞርቱ አስታወቀ። አዲስ ማለዳ ያነጋገረቻቸው የድርጅቱ ከፍተኛ ባለድርሻ ዲንቁ ደያሳ እንደገለፁት ‹‹ለጊዜው ሪዞርቱ ለምን እንደተዘጋ አላውቅም። እኔ……

Read More

ልደቱ አያሌው የሽግግር መንግሥትን የሚመለከት አዲስ መጽሐፍ ጻፉ

ልደቱ አያሌዉ ‹‹ለውጡ ከድጥ ወደ ማጡ›› የተሰኘ አዲስ መጽሐፍ ጽፈው የመጨረሻ ረቂቁን ማጠናቀቃቸው ታወቀ። የሽግግር መንግሥትን በሚመለከት ሰፊ ትንታኔ እና ገለጻ የያዘው አዲሱ መጽሐፍ፣ ‹ብሔርተኝነት፣ ጽንፈኝነትና የአመራር ድክመት የተቀየደች አገር” ሲሉ የመጽሐፋቸዉን ጽንስ ሐሳብ በንዑስ ርዕስነት ከፋፍለው አስቀምጠዋል። በ104 ገጾች……

Read More

በተጭበረበሩ ቼኮች ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ ተመዘበረ

ከ2011 የመጨረሻ ወራት ጀምሮ በተደረገ ክትትል በቼክ ማጭበርበር ከ100 ሚሊዮን ብር በላይ መመዝበሩን ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ለአዲስ ማለዳ አስታወቀ። በተደረገው ክትትልም በቁጥጥር ስር ውለው ክስ የተመሰረተባቸው 30 የክስ መዝገቦች እንዳሉ የተገለጸ ሲሆን፣ የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑንም ጨምሮ ገልጿል።……

Read More

በአዲስ አበባ የታክሲዎችን እንቅስቃሴ የሚቆጣጠር መተግበሪያ ወደ ሥራ ሊገባ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የሚንቀሳቀሱ የከተማ ታክሲዎችን እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር የሚረዳ ‹አዲስ ጉዞ› የተሰኘ አዲስ መተግበርያ በሥራ ላይ ለማዋል በሂደት ላይ እንደሆነ ተገለጸ። አዲሱ የታክሲዎች መቆጣጠሪያ መተግበሪያ የትራንስፖርት አመራር ስርዓት (TMS) አገልግሎትን የሚያሳልጥ ሲሆን፣ ከ15 ቀን በኋላ ተግባራዊ ለማድረግ ዝግጅቶች……

Read More

ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ ያደረጉ 12 ትምህርት ቤቶች ላይ ምርመራ ተጀመረ

የኢትዮጵያ ንግድ ውድድርና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን ያለ አግባብ የተማሪዎች የትምህርት ቤት ክፍያ ጨምረዋል በተባሉ 12 ትምህርት ቤቶች ላይ ምርመራ ጀመረ። ከፍተኛ ችግር አለባቸው ተብለው በተለዩና በአዲስ አበባ በሚገኙ 12 የግል ትምህርት ቤቶች ላይ የወላጆች ኮሚቴ እና የተማሪ ወላጆች ባቀረቡት ቅሬታ……

Read More

ብሔራዊ ባንክ አዲስ የወርቅ ግብይት ስትራቴጂ እያዘጋጀ ነው

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በየዓመቱ እያሽቆለቆለ የመጣውን የወርቅ ገቢ ለማሻሻል እና ሕገወጥ የወርቅ ግብይቱን ለመቆጣጠር አዲስ የወርቅ ግብይት ስትራቴጂ እያዘጋጀ መሆኑን አስታወቀ። አዲስ በሚዘጋጀው የወርቅ ንግድ ስትራቴጂ ላይ የወርቅ ግብይት ዋጋ ላይ ማሻሻያ እንደሚደረግና እንዲሁም ወርቅ በሕገ ወጥ መንገድ ከአገር የሚወጣበትን……

Read More